„የኛ„ ዓለም ሲያየው ! THE GIRL EFFECT
Posted in ኪነ፥ጥበብ
Posted in ባህላዊና ማህበራዊ /Cultural & social, ኪነ፥ጥበብ
ለመዝናናት –
ሙዚቃ ሲንቆረቆር….
ከፖለቲካ ውጭ (ይህ ነው የሰው ልጆች ሌላው ችሎታ) ከእሱም ከፖለቲካው የበለጠ የአንድ አገርን ሕዝብ ውስጣዊ ሰሜት ቀሰቅሰው የሚያስተሳስሩአቸው ብዙ ነገሮች አሉ። አንደኛው አለጥርጥር ልብን የሚነካው ሙዚቃ ነው። ሙዚቃ ደግሞ በስፋትና በጥልቀቱ ድንበርም አልፎ ሄዶ ( አብዮታዊ መዝሙር እኮ እዚህ ግባ የማትባል ውስን ነገር ናት እሱዋን እንርሳ!) የሰው ልጆችን የበለጠ ያቀራርባል።ያስተሳስራል። ሌላው ሁለተኛው ግሩም ልብ- ወለድ የፍቅር ድርሰትና ድራማ ነው። እነሱ እንዲያውም „ዩኒቨርሳል“ ናቸው። ፊልም አለ። ግጥም። እስክስታና ጭፈራ…
ቀደም ሲል በአለፈው ዓመት ደስ የሚለውን „አቤት አቤት…“ የሚለውን የወጣቶች ጨዋታ ሰምተናል። አሁን ደግሞ እነሱን የመሰሉትን አዲሱን „የጃኖ ባነድ“ ሙዚቃ በዚህ በመስከረም ወር አዳምጠን እጅግ ደስ ብሎናል። ዱሮውንም -ይህ ባህል በዚያ በደርጎች አብዮታዊ መዝሙር ተቀየረ እንጂ- ዱሮውንም በመስከረም፣ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በምሽቱ ላይ ስንት አዳዲስ ሙዚቃዎችን የምንሰማበት ቀን ነበር። አሁን በአዲሱና በወጣቱ ትውልድ ይህ ነገር እንደገና መጀመሩ ደስ የሚያሰኝ ነው። ምን ይላሉ እነዚህ ወጣቶች?
“አይራቅ የምትመጪበት ቀን
አይራቅ የምትመጪበት ቀን
አይራቅ የመገናኛው ቀን
አይራቅ የምትመጪበትቀን
ፀሃይ ካይኖቼ ስትጠፋ
ነገን ስጠብቅ ሁሌ በተስፋ
ያ ነገም ነግቶ ይመሻል
ሁሉ መጥቶ አንቺ ብቻ ቀርተሻል
አይራቅ….(Chorus)”
http://janoband.com/fr_home.cfm
መልካም መዝናናት….
Posted in ኪነ፥ጥበብ
“ጃኖ” ውን ልበሱ
እኛ እነዚህን ወጣት ያገራችን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ተዋናዮችን ስንተዋወቅ ደስ ብሎናል! የእነሱን ውብ አዳዲስየሙዚቃ ውጤቶች እያየንና እየሰማን የምናደንቀው፣ ለነጻነትና ለአዲስ ጥበብ ላዲስ ሕይወት የሚያደርጉት ጥሪ ሆኖም እንዲሰማን ስላደረገን ነው። በመሆኑም፣ ላንባቢዎቻችን እንዲተዋወቋቸው፣ እንዲያደምጧቸውና የነጻነቱ መንፈስ እንዲጋባባቸው እዚህ እንጋብዛለን!
እኛም፣ በያሬድ ቅዳሴና ዜማ አድገን ነፍሳችንን አውቀን፣ ከሌላው ዓለምና ከአዲሱ ዘመን ጋር ስንገናኝ፣ የነጻነትን መንፈስ በጊዜያችን ያበሰሩልንን፣ ከብዙ በጥቂቱ፣ የነጂሚ ሄንድሪክስን የነሳንታናን የነቢትልስንና ሮሊንግስቶንስን ቅኝት እያስታወሰን፣ እኛንም መለስ አርጎ ስለሚወስደን ብቻ ሳይሆን፣
የዚህ ዓይነት ተውኔትና ሙዚቃ ምን ያህል ነጻ የሆነ የሕሊና መንፈስ እንደሚያበጅም ስለሚገባን ነው!
ምን ያህል አእምሮንም ከፍ ወዳለ ቦታ ላይ እንደሚገፋውና እንደሚያደርሰው ስለምናውቅ ነው!
ስለሆነም፣ ይህን በሀገራችን የሙዚቃ ቅኝት ላይ የተመሰረተ አዲስ የኢትዮጵያ ተወዛዋዥ ቡድንን / Ethiopian rock & roll Band/ በርቱ፣ አዎ ደስ ደስ ይበላችሁ እንላለን! ደስታን የሚያውቅ ወጣት፣ ክፉ አዋቂ ሊሆን አይችልም!
እንኳን ደስ ያለህ እንላለን!
*
እንደውነቱ ከሆነማ፣ በኪነቱ አካባቢ ያሉትን ሌሎችንም (ለምሳሌ እንደ ወጣቱየሳሙኤል ይርጋ የኢትየጵያ ጃዝ ቅኝትና የግርማ ይፍራ ሸዋን ዓለም፥አቀፋዊ የክላሲካል ሙዚቃ ስኬት) ስናስተውል፣ እዚያው በዚያው የሚንደፋደፈው የፖለቲካው ማህበራዊ ክፍል ብቻ እንደሆነም እንገነዘባለን። ከገባበት የጦርነትና የአፈሙዝ ማጥ መላቀቅ ተስኖት፣ የነፃነቱን መንፈስ ሳያስተናገድ፣ ግማሽ ምዕተ ዓመት ትንሽም እምበር ሳይል አለፈ!
ለዚህም ይሆናል እነ ” ጃኖ “
” አይራቅ! አይራቅ! ” ሲሉ የሚጣሩልን!
ይሉናል! ይነግሩናል!
______________
እንዲያም ስለሆነ እንኳን ደስ አላቸው፣
እኛም በጥቂቱ እናወድሳቸው!
ኢትዮጵያን ከፍ አርገው፣
ኪነት ሙዚቃውን በማሻገራቸው…
ወጣት ደስ እያለው፣ እምበር እምበር ሲል
ሰማይን ፈልጎ ከፍ እያለ ሲዘል
በሙዚቃ ምሰጥ በኪነት ስነ ሀይል
ያስታውቃል ከሩቅ ነፃነትን ይሻል
“አይራቅ አይራቅ አይራቅ“ — ነፃነቱ ይላል!!
ጃኖ – ውን ልበሱ ….. ነፃነት ይመጣል፣
ወጣት ነፃ ሲሆን፣ „ጃኖን ባንድ“ ይመስላል!
*
ባለጃኖዎቹ፣ እንኳን ደስ ያላችሁ
ለዚህ ስኬታችሁ
ኢትዮጵያን አስጠሯት በሕይወት ፍቅራችሁ!
እውነት “መሄድ መሄድ፣ መ ሄ ድ “፣
መጓዝ ነው መፍትሄው ለነፃነት መንጎድ
ወጣት አይል አዛውንት
ሙዚቃችሁ ውበት ፈንጠዝያ ሕይወት!
ከፍ ባለው ሕሊና፣
*
እንኳን ደስ አላችሁ፣
እስቲ እናድምጣችሁ…
እስቲ እንያችሁ….
ተወዛወዙበት፣ ምስጋና ይግባችሁ!
እኛ እንኳን ዳር ቆመን እናመስግናችሁ!
*
http://janoband.com/fr_audio.cfm
****
አዲስ ገሰሰ
The Manager Introducing Jano Band
http://www.ethiotube.net/video/22907/Jano-Band–Who-are-they
*
—————————————————-
አስተያየት ለመስጠት / Comments
——————————–
——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013
http://www.africa.upenn.edu/Smithsonian_GIFS/Boghossian.gif
እስክንድር፣
በኪነ ጥበብ ፀጋው፣ ማዕከሉ ላይ ያለችውን ሰላም ለማግኘት፣
በዘመናችን ያለውን አምባ ጓሮ፣
ከንቱ ዕልቂትና ውዳሴ ሲያስመዝግበን ይሆን ?
አዎ ሰሚ አእምሮ ካገኘ!
____
Boghossian was born on July 22, 1937 in Addis Ababa, at the time the capital of the Italian colony Italian East Africa, one and half years after the Second Italo-Abyssinian War.[1] His mother, Weizero Tsedale Wolde Tekle, was Ethiopian.[1] His father, Kosrof Gorgorios Boghossian, was a colonel in the Kebur Zabagna (Imperial Bodyguard) and of Armenian descent.[1] Kosrof’s father, Gregorios Boghassian, an Armenian trader, had established a friendship with Emperor Menelik II and worked as a traveling ambassador in Europe on behalf of the Emperor.[4]
Boghossian’s father was active in the resistance against the Italian occupation and was imprisoned for several years when Boghossian was a young child.[1] His mother had set up a new life apart her children and although both he and his sister Aster (Esther) visited their mother frequently, they were raised in the home of their father’s brother Kathig Boghassian.[4] Kathig, who was serving as the Assistant Minister of Agriculture, together with other uncles and aunts brought them up during their father’s imprisonment.[4]
He attended a traditional Kes Timhert Betoch kindergarten where he was taught the Ge’ez script.[1] In primary and secondary school, he was taught by both Ethiopian and foreign tutors and become fluent in Amharic, English, Armenian and French.[1] He studied art informally at the Teferi Mekonnen School.[5] He also studied under Stanislas Chojnacki, a historian of Ethiopian art and watercolor painter.[5]
https://www.google.de/search?q=Skunder+Boghossian-and-more
SKUNDER TRIBUTE
Celebration of Art & Culture
________
—————————————————-
አስተያየት ለመስጠት / Comments
——————————–
——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013
Posted in ኪነ፥ጥበብ
ፕያሳ ማሃሙዴ ጋ ጠብቂኝ!
(ለደራሲ መሀመዴ ሰሌማን፣ ከከበረ ምስጋና ጋር)
ማሃሙዴ ጋ ጠብቂኝ! (ከመሀመዴ ሰሌማን)
ማሃሙዴ ጋ ጠብቂኝ!
(መሀመዴ ሰሌማን)
_
ስብሓት ‹‹ትኩሳት›› ብሎ በጠራው መጽሐፉ ጀርባ ላይ ምን አለ? “ወጣት ሁን” አለ፡፡ ቢመርህ ‹‹ሪቮለሽን›› ታስነሳለህ፣ እጅግ ቢመርህ ራስህን ታጠፊለህ…፡፡ ለማንኛውም ወጣት ሁን፡፡ እኔ ግን እልኻለሁ፣ ወጣት መሆኑን ሁን፣ ነገር ግን ራስህን ከማጥፊትህ በፉት ፒያሳ ሂድ፤ ሀሳብህን ልትቀይር ትችላለህና፡፡ ለመሞትም ቢሆን የፒያሳን ያህል መልካም ሰፈር የለም፡፡ ቀባሪ አታጣም፤ በፒያሳ ሰው ባያይህ ማዘጋጃ ያይኻል፡፡ ለመሞትም ለመኖርም ስታስብ ፒያሳ ሂድ፡፡
—————————————————-
አስተያየት ለመስጠት / Comments
——————————–
——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013
Posted in ነፃ አስተያየት/Free Opinions, ኪነ፥ጥበብ
“The history of the Ge’ez writing system is not as easy to trace as the Roman, owed primarily to widely accepted but inaccurate scholarship based on Euro-centric assumptions. As Amadou-Mahtar M’Bow has written there was a refusal to see Africans as creators of original cultures which flowered and survived over the centuries in patterns of their own making and which historians are unable to grasp unless they forego their prejudices and rethink their approach.”(see below, our italics)
ባጭሩ የግእዝ ፊደል ስረ መሰረት ሶስት ገጽታዎችን፣ የሚያመለክት አጭር
ጥናት ነው። ማለትም ግእዝ
1ኛ ሥዕላዊ ገጽታ
2ኛ ርዕዮታዊ/ሃሳባዊና
3ኛ ሰማያዊ/ መንፈሳዊና መለኮታዊ ገጽታ እንዳለው፤ በዚህም ከዘመን መቁጠሪያ ጋር በተያያዘ አልፎም ከኮከቦች አቀማመጥ ቀምር ጋር
የተመላከተና የረቀቀ መሆኑን ያሳያል።
i.e. “Astrography, or the charting of the stars and hence, the calendar, is the third property of the Ge’ez system. The system, with it’s 26 classes and 7 variations provide its total of 182 syllographs. One hundred and eighty two, being half of 364, represents a half-year or one equinox.”
….
“Each of the syllographs have a corresponding number value from 1-5600.The number values associated with each syllo graph also contains codes of the Ethiopian knowledge (mystery) system. “
Read More:
ማይስትሮ ግርማ ይፍራሸዋ
ከኪነ፥ጥበብ ዓለም፤ ማይስትሮ ግርማን፣ በዶክተር አሸናፊ ከበደ ፈለግ ሲጓዝ፣ እስቲ እንተዋወቀው!
ንውዩን ፍለጋ ብቻ፣ የቆየውን እንደማይሆን እናድሳለን፣ በማለት፣ ያልበቁ ባለ ሙያዎች፣ ጆሮአችንን እንደሚያደክሙት ሳይሆን፣ እንደ መንፈስ መነቃነቅ በሚቃጣቸው ጣቶቹ፣ ፒያኒስት ግርማ ከሙዚቃችን ውበት ጋር ያገናኝናል። ውበት ይጋብዘናል !
ዩትዩብ ውስጥ በድረ ገጽ ላወጡልን ባለጉዳዮች ምስጋን እያቀረብን፣ እነሆ ለእናንተም ይሁን፥
***
ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements > Le’Aimero’s Disclaimer
Posted in ነፃ አስተያየት/Free Opinions, ኪነ፥ጥበብ
እኔ፣ ከ እኔ ፣ ወዲያ
ዛሬ ጊዜ መቼም ሳጥን የሚወዱ ዓይነታቸው ብዙ ነው።
አንድ ዓይነት ሁሉንም የሚያደርጋቸው ግን አንድ ጉዳይ አለ።
ሳጥን ውስጥ መቅረት ስለሚፈልጉ፣ ሁሉም ከኔ ወዲያ ባዮች መሆናቸው ነው።
እስቲ አማርኛችንም ወደ ሳጥን (1 ከመላኩ በፊት፣
የለም እንዳውም እንዳይላክ ስንል እንናገርበት፥
*
እኔ፣ ከ እኔ ፣ ወዲያ
ነጋ ጠባ እኔ ማለት
ትልቅ ምንጩ ፍርሃት
የሚ-ኖረው ለጥፋት፣ በጥፋት፤
በድክመት፣ ያለምነት፤
ላይቀር ሞት።
እየማለ ሲገዘት
ምኑን አወቆ ስለ መብት፤
ለመሆኑ በዛ ማዶው
መች አ-ርቆ አሰበው፣
ግማሽ ጎኑ አምላኩ ነው፤
ባምባው ብቻ የማይገነው፤
በሁሉም ቤት የሚ-ሆነው፤
ለ ዝንተ ዓለም የሚዘልቀው።
*
ወጣ ብንል ከራስ ሳጥን፣
ብንተያይ ቆም ብለን ፣
አይ ሲያምርብን በዛ ብርሃን፣
በአንድነት፣
ፍሬ፥ነገር ሲወጣን።
ቁም፥ነገሩ ሲሆነን።
*
![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() ![]() |
http://www.goolgule.com/the-i-box/
ባገራችን የባህልና ታሪክ ቅርስ የሆኑትን ሁሉ ለማፈራረስ የመጣብንን የባዕድ ሥልጣኔ አባዜ ለማመልከት ነው። (ፎቶ: በጸሐፊው የተላከ)
*
———————————————————
ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements > Le’Aimero’s Disclaimer
Posted in ሌሎች / others, ነፃ አስተያየት/Free Opinions, ኪነ፥ጥበብ
http://en.wikipedia.org/wiki/Ashenafi_Kebede
*
የሚከተሉት ዶኩመንታሪ ተንቀሳቃሽ ስዕሎች ያስተዋውቁናል።
ከ ኢቲቪ / ETV፣ ዩ ትዩብ ድረ፣ ገጽ ላይ የተገኘ፣ ለደራሲዎቹ ከመስጋና ጋር፤ 1)
****************
http://www.youtube.com/watch?v=U-cN-QQc4Ss
http://www.youtube.com/watch?v=JSKrTxuvmJI
http://www.youtube.com/watch?v=wq6Sg-KSDno
************************
ለ አእምሮ መጽሔት፣ ወደ ዋናው ገጽ ለመመለስ…………………..
*
አድራሻችን ፥ Public Email
አስተያየት እንዲሁም ለአእምሮ መጽሔት ጥናቶችና ጽሁፎች ለማበርከት ፥ የሚከተለውን አድራሻ ይገልገሉ፥
Public Email
Verified Services
—————————————————————————————————————————
ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements:- Le’Aimero’s Disclaimer
1) እነዚህን ስዕሎች እዚህ በመውጣታችን የባለቤትነት መብታችሁን ከተላለፍን፣
እንድናነሳው እንዳስታወቃችሁን እንሰርዘዋለን!
******************************
Posted in ኪነ፥ጥበብ