መለያችን

የክንፎቹን ምስል፣

ለመታያችን-ለመለያችን፣ ለምን ይሆን የመረጥነው !

 Laimero-frame-logo2

መለያችን (PDF)

*

መቃ ብዕር ወይም የአሞራ ወይም ደግሞ የአውራ ዶሮ ይሁን የእርግብ ላባ፣ ከቀለም ብልቃጥ ጋር አንድ ላይ፣ እነዚህ  ሁለቱም፤ ሶስቱም  ነገሮች፣  የቀለም ሰዎች ሙያየጸሓፊዎችና የደራሲዎች፣ ወይም  ደግሞ፣ ሁላችንም እንደምናውቀው፣ የጋዜጠኛ ምልክቶች ናቸው።

a_Schreibfeder

እኛም  አሳታሚዎቹ መርጠን የወሰድነው ምልክት፣ በአንድ በከል ሲታይ ከዚሁ ጋር፣

በትክክል ለመናገር  በጥብቅ የተያያዘም ነው።

*

እንደ ምልክት ፣ ሳያውቁም ሆነ አውቁው እንደስቀመጡት አርማ ቁልጭ ያለች ማብራሪያ ለዚያች ጉዳይ፣ በአሀኑ ሰዓት፣ የሚሰጥ ነገር የለም።

መቼም አንድ አርማ ፣ ለአንድ አሳታሚ የግል ድርጅት ሆነ፣ ወይም ደግሞ አንድ አላማ ለአለውና ለሚከተል፣ ለዚያ የፖለቲካ ፓርቲ፣…ነጋዴም ሊሆን ይችላል፣….እሱ መርጦ፣ እንደ ተሸከመው፣ ግንባሩ ላይ እንደ ለጠፈው አርማ ፣ ያ ድርጅት ማን መሆኑን በትክክል የሚያሳይና የሚገልጽ ወይም አለቃላት የሚያብራራ፣ ሌላ ነገር ፣ በዚህ ዓለም ላይ የለም።

የጀርመኑ ማርቼዲስ ፣… ወይም አውዲ፣ ቢኤም ደብሊው፣ ወይም …ቮልክስ ቫገን፣ የእንግሊዙ፣ ወይም የጀርመኑ ሮልስ ሮይስ፣ ….የጃፓኑ ቶዮታ፣ የፈረንሳዩ ስትሮዋን፣ ወይም ፔጆ….እነዚህ ሁሉ መርጠው የያዙት ምልክቶች፣… ለመኪናዎቹ ጥራት፣ ለጥንካሬአቸው፣…ለክብራቸው፣ ብዙም ማውራት የማያስፈልጋቸው፣ ማንነታቸው፣ ማን መሆኑን የሚገልጹበት አርማዎች ናቸው።

„ማጭድና መዶሻ „ ምንም እንኳን እንደምናውቀው፣ የላብ አደሩና የገበሬው አንድነትን፣ ሕብረትን የሚገልጹ ቢሆንም፣ ዞሮ ዞሮ ከአለፉት ታሪኮች እንደተማርነው፣ የጥቂት „እኛ ለእናንተ የምትፈልጉትን፣ የሚስማማችሁን ነገር ሁሉ፣ እኛ ብቻ፣ እናውቃላችሁዋለን „ የሚሉ ፣ „ጤናማ ይሁኑ ወይም ዕብዶች፣… ምሁሮች፣ ወይም ወታደሮች“ ምልክት ሁኖ እንደቀረ ፣ ሁላችንም ከዚህ ሁሉ አመት በሁዋላ፣ ከቀመስናቸው ግንዛቤዎች፣ ልምዶች፣ በደንብ አድርገን፣ ዛሬ እናውቃለን።

እንዲያውም ይህ ምልክት በሰሜን ኮሪያና በቻይና ብቅ ያሉ ብልጦች እንደሚያስተምሩን ከሆነ ደግሞ፣ የዘርግንዱ ሳይነካ እንደ ዘውድ አገዛዝ ሥልጣኑ ከልጅ ልጅ ወደታች መስመሩን ጠብቆ በቀጥታ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚተላለፍበት „የዙፋን ምልክት ነው።“

ስለ ዘውድና ዙፋን ከአነሳን አይቀር፣ እነሱ እንኳን ሳይቀሩ ከጊዜውጋር ተራምደው፣ ቢያንስ በጃፓን፣…በስዊዲን፣ በዴንማርክ፣ በኒዘርላነድና በእስፔን…ከሥልጣን ርቀው ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ፣ ለዲሞክራሲ ሥርዓት ያላቸው አመለካከት፣ አስተያየትና አክብሮት፣ „አብዮተኛ ነኝ ብሎ ከሚፎክረው የአፍሪካ ተራማጅ፣ ኮሚኒሰት“ በስንትና ስንት ኪሎ ሜትር፣ እነሱ አጣፍተውት፣ እንደሚሄዱ አሁን መናገሩና ማውራቱ፣ ለእኛ ከንቱ ነው። የእንግሊዞቹማ፣ ነገሥታት ነገሩ ገብቶአቸው፣ ሥልጣኑን ከአስረከቡ፣ ጊዜው በጣም ረጅም ነው።

„ዘውድ“ ሆነ „ማጭድና መዶሻ „ጊዜው አልፎባቸል። የሚከተላቸውም ሰው አሁን የለም። ግን ! ጠበንጃና ዘንባባ፣ የስንዴ ነዶና ዝናር፣ ቀለሃና ድግን መትረየስ፣ እነሱ ምልክቶች ደግሞ ምንድናቸው?

አትታለሉ! እነሱም፣ ሌላ ነገር ይምሰሉ እንጂ፣ የጥቂት አምባገነን፣ ምልክቶች ናቸው።

ታዲያ እኛ የመረጥነው የአሞራ ክንፍ፣ ወይም የዶሮ ይሁን የዕርግብ ላባ፣ የለም፣ እንዳውም የአማልክት ክንፍ፤ ወይም ደግሞ፣ መቃ ብዕር፣ እሱ ምንድነው? ምን ለማለት? ምን ለማሳየት ተፈልጎ ነው?

ይህ መርጠን እኛ የወስደነው አርማ፣ በሁለት መንገድ፣ በሁለት አቅጣጫ፣ „የመንፈስ ቅዱስ“ ምልክት ነው።

በአንድ በኩል ከእኛ ከሰው ልጆች በላይ የሆነ (የሰው ልጅ ዕውቀት ውስን ነው) አንድ -እናንተ የፈለጋችሁትን ስም ልትሰጡት ትችላላችሁ- ከእኛ አእምሮ በላይ የሆነ፣ የበለጠ ጥልቅ ያለው፣ ዕውቀት ያለው፣ ቅዱስ አምላክ፣…. መንፈስ ቅዱስ ከእኛ በላይ አለ ለማለት ነው።

ሁለተኛው ትርጉም፣ የተለያዩ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች፣ እምነቶችና አቋሞች፣ የሚቀያየሩ ዝንባሌዎችና ግምቶች ፣ የሚፎካከሩ እኔ እሻላለሁ የሚሉ አማራጭ መፍትሔዎች፣ አንዱ ተነስቶ ሌላውን በሰይፍና በብረት አሳዶ ሳያጠፋውና ሳያንቀው፣ ተቻችለው፣ ተከባብረው፣ ተደማማጠው፣ ተወቃቅሰው፣ ተማምረው፣….አብረው ሊኖሩ ይችላሉ፣ የሚለውን „ቅዱስ ሐሳብ፣ ቅዱስ ተመክክሮ…ቅዱስ መንፈስ፣…“ በእኛ መካከል ለማራመድም ነው።

በሌላ ቋንቋ፣ የማንንም ሰው ነጻ፣ የሆነውን… የመናገር፣… የመቃወም፣…የመተቸት፣ የመመራመር፣ የመጠየቅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ የመጻፍ፣…. ሐሳቡን የመቀየርና ሐሳቡን የማስተማር ሆነ የማስራጨት ሙሉ መብቱን፣ ነጻነቱን – ማንንም ሳይፈራና ሳያጎበድድ፣ ኮርቶ፣ በዚህ በያዝነው በ21ኛው ክፍለ-ዘመን፣ ሊተነፍስ ይችላል የሚለውን ሐሳብ፣ በዚህ አእምሮ በሚባለው መጽሔት፣ ለማብሰር ነው።

ኢትዮጵያ እራሱዋ ወዳና ተስማምታ፣ አንዳዶቻችን ሳንፈጠር፣ ገና ዱሮ የፈረመችው የሰብዓዊ መብት አዋጅ ግሩም የሆነ ነገር አሰቀምጦልናል። እሱም:- ባርነትን ይከለክላል። “ „…ማንም ሰው፣ በባርንት ወይም …በግዴታ አገልጋይነት አይያዝም!“ ይላል። „ በሕግ ፊት ማንም ሰው፣ መብቱ የታወቀ ነው..“ ቀጥሎ ይላል። ወረድ ብሎ „….ማንም ሰው አስተያየት የመስጠትና ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነትና መብት አለው፤“ ይላል። „የሕሊናና የሃይማኖት ነጻነቱን፣ ….የንብረት ባለቤትነት መብቱን፣….የመሰብሰብ፣ የመማርና የመመራመር መብቱን፣ ይኸው መግለጫ ጠቅሶ፣ በአንቀጽ አንዱ ላይ፣“ የሰው ልጆች ሁሉ በነጻነታቸው፣ በክብራቸውና በመብቶቻቸው እኩል ሆነው የተፈጠሩ ናቸው።“ ይላል።

እኛ በዚህ መጽሔት ሙሉ ሰብዓዊ መብታችንን ፣ ሙሉ ሰብዓዊ ነጻነታችንን፣ ከዛሬ ጀምሮ እንደማንኛውም ነጻ ሰው አውጀናል።

**********

„….አሕዛብ ሁላቸሁ ይህን ስሙ፣ በዓለም የምትኖሩም ሁላችሁም አዳምጡ፣ ዝቅተኞች ከፍተኞች ባለጠጎችና ድሆች በአንድነት። አፌ ጥበብን ይናገራል፣ የልቤም አሳብ ማስተዋልን።  ጆሮዬን ወደ ምሳሌ አዘነብላለሁ፣ በበገናም ምሥጢሬን እገልጣለሁ።“

ዊሊያም ሼክሽፒር መቃብር ላይ ተገልጦ የተቀመጠ የዳዊት መዝሙር ፣ ም.48(49)

laimero-boardeaux-fire-slant-bordeaux

*

*——————————መጀመሪያ ገጽ ለመመለስ—————————–laimero-boardeaux-fire-slant-bordeaux

a_Schreibfeder

*

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements > Le’Aimero’s Disclaimer

leaimero-reg-logo © ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s