የተከለከለ መጠሪያ፤ የማይረሳ ፍጅት :- „ቱቲስ እና ሁቱ“

የተከለከለ መጠሪያ፤ የማይረሳ ፍጅት :-

„ቱቲስ እና ሁቱ“

የተከለከለ መጠሪያ፣  የማይረሳ ፍጅት :- „ቱቲስ እና ሁቱ“

ተከለከለ መጠሪያ የማይረሳ ፍጅት :- „ቱቲስ እና ሁቱ“
የእርስ በእርስ ጦርነቱ የፈነዳው ሳይታሰብ ነው። እነሱም ይህ ይሆናል ።ይህ አንድ ቀን ይመጣል፣ ብለው አላሰቡም።

አንድ ቀን አንዱ ተነስቶ ሌለውን በቆንጨራና በቢላ በመጥረቢያና በሳንጃ የገዛ ጉረቤቱን ዘመዱን ሚስቱንና ልጆቹን አማቸን ጭምር ይገድላል፣ያርዳል በእሱ እጅ ይሞታል/ ትሞታለች ነፍሱንም ያጣል ብሎ ያሰበ ሰው አልነበረም።


ትንሽ ቀስቃሾች የታጠቁ ወታደሮችና ሚሊሻዎች እንደ ዋዛ የጀመሩት ፍጅት በሁዋላ ተቆጥሮ እንደተሰማው ሁሉንም አሳብዶ በመጨረሻው ከስምንት መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑትን የአገሪቱን ሰዎች ሕይወትና ነፍስ ይዞ ሄዶአል።


በቤታቻውና በቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ሰዎች እሳት ተለኩሶባቸው ጋይተዋል። ሲሸሹ በጥይት እንደ አውሬ ታድነዋል። መሮጥ የማይችሉት ተይዘው ታርደዋል።


ማን ምን እንዳደረገ በሁዋላ ፍርድ ቤት አንዳንዶቹ ተይዘው ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል።


ጥላቻውና መዘዘኛው የዘር ልዩነት የተጀመረው በቤልጅጎቹ የከፋፍለህ ግዛ ተንኮልና ሥራ የቅኝ ግዛት ዘመን ነው።

ከመሬት ተነስተው እንደፈለጉት በ1920 አጋማሽ ላይ አንተ „ቱሲ“ አንተ ደግሞ „ሁቱ“ ብለው ሰውን በዘር ግንድና በአጥንት ቆጠራ እዚያ ሽንሽነውና ከፋፍለው መታወቂያ ወረቀታቸው ላይ ይህን የዘር መለያ ምልክታቸውን ጽፈው ኑዋሪውን አናክሰው አለያይተዋል። ጣሊያንም በኢትዮጵያ ሞክሮ ሳይሳከለት ቀርቶአል። burundi+


ይህ ሆን ተብሎ ቀደም ተብሎ የተረጨው መርዝ ሥር ሰዶ ሰውን በሩዋንዳ የዛሬ 20 አመት አፋጅቶአል።
አሁን በሩዋንዳ ሕዝቡን በዘር መከፋፈልና በመታወቂያው ወረቀት ላይ „ሁቱ እን ቱሲ“ ብሎ ለይቶ መጻፍ በህግ የሚያስቀጣ በመሆኑ እዚያ ተከልክሎአል። ሁሉም አሁን ረዋንዳ ሩዋንዳዊ ናቸው።


በደቡብ አፍሪካም የአንድን ሰው ዘር መታወቂያ ወረቀቱ ላይ መጻፍ እዚያም እንዲከለከል እነ ማንዴላ አድርገዋል።

በዘር እና በሃይማኖት በመደብና በከረረ አይዲኦሎጂ መበጣበጥ መጨረሻው ማለቂያ የሌለው ፍጅት ነው።

ለዚህም 20ኛው ክፍለ ዘመን ምስክርም ነው።ፋሽሽቶች አይሁድንና ሲንቶወችን ጥቁሮችና ደካማዎችን ፈጅተዋል።

በመላው ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን የሩዋንዳ ፍጅት ሳይረሳ በሕሊና ጸሎት ሰው ሁሉ አስታውሶታል።


የሚያስፈራው የሚቀጥለው ሁለተኛው ሩዋንዳ ነው።

ማን ይሆን?… ማን ትሆን?

ከመካከለኛው አፍሪካ አስፈሪ ዜና ይሰማል።

ሌላም ቦታ በአፍሪካ ወደዚያው የሚያመሩ አገሮች ጥቂት አይደሉም ይባላል።

እነማን ይሆኑ? የዕብዶች ዓለም!

 

……

logo-circ-reg

—-

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s