ጠንካራ ክንድና ነጻነት

ጠንካራ ክንድና ነጻነት

leading-leaders

ው ምን እንደሚፈልግ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው። በዚያ ሲሉት በዚህ ይታለል። ያን ሲያቀብሉት እጁ ላይ ያለውን ጥሎ እንደ ህጻን ልጅ ያኛው ያምረዋል። ይህን ሲሰጡት ጨምር- አልበቃኝም ይላል። ሲበዛበት ደግሞ ቋቅ ሲለው ይ… ሰው አስቸጋሪ ነው። እንደ ሰው አስቸጋሪ ፍጡር የለም።

እሩቅ ቦታ ሳንደርስ በቅርቡ በተካሄደው በቱርኩ ኤርድዋን በሩሲያው ፑቲን በእነሱ እርምጃ ያልተደሰተ በተቃራኒው ያልተበሳጨ ሰው የለም። የግብጹ ሙርሲና ፊልድ ማርሻል አዚዚ አሉ።

ሁለተኛውን ትተን የመጀመሪያዎቹን እንውሰድ።

„ፑቲንን ለሩሲያ ኤርድዋን ለቱርክ እግዚአብሔር መርቆ የሰጣቸው መሪዎች ናቸው!“ ብዙ ሰዎች ይላሉ። በተለይ ቪላዲሚር ፑቲን „ትልቅ ቦታ“ በአንዳንድ ኢትዮጵያኖች ዘንድ አላቸው።

ከልብ ይሁን ከምኞት፣ እነሱን ከገቡበት የሚያወጣቸው ሰው አጥተው ይሁን ወይም ተመሳሳይ ሰው ናፍቀው፣ ወይም ከአለፉት ታሪክ ተነስተው -ሁሉም በየፊናው የሚሰጠው አስተያየት የተለያየ ነው- ምኑንም ከመገመት በላይ ይህ ነው ብሎ አሁን መናገር አይቻልም። ግን ነገርን ለመረዳት ዓለምን በሌላ ዓይን ለማየት ታሪኩ ይሰጣል።
በሙስና እና በዘመድ ሥራ „ከእነ ቤተሰባቸው ተጨማልቀዋል “ ተብለው በብዙ ሰዎች ዘንድ የተከሰሱሱት የቱርኩ ጠቅላይ ሚንስትር በምን ተአምር ይሁን በምን- እንተርኔቱንም ዘግተውም ስልክም ተቆጣጥረው – እሳቸውና ድርጅታቸው ያ ሁሉ ሆኖ „በሕዝባቸው ድጋፍ “ በ45% እንደገና ተመርጠዋል።

በቅርቡ የተካሄደውን ምርጫ አጭበርብረዋል የሚሉም አልጠፉም። ከክሪም ወዝግብ በሁዋላ ፕሬዚዳንት ፑቲን „በሕዝባቸው“ ዘንድ ያልተጠበቀ ድጋፍ እሰከ 70% ድረስ አግኝተዋል።

ምንድነው ምክንያቱ?

ምንድ ነው ? …የሰዎችን ፍላጎትና የልብ ትርታቸውን አንዴ ከፍ የሚያደርገው ሌላ ጊዜ የሚያሸፍተው ነገር? ሰዎችን እጃቸውን ይዞ ጥቅጥቅ ከአለ ጫካ፣… ሰው ከማይደርስበት በረሃ እና ከገደል አፋፍ ወይም ከሚነድ እሳትና ከመከራ ከጥፋትና ከውድቀት እነሱን ጎትቶ የሚያወጣቸው „መሪ“ ከሙሴና ከአሮን ታሪክ ወዲህ እነሱ እንደ ሚሹ እንደሚፈልጉ እንደሚመኙ ብዙዎቻችን በደንብ እናውቃለን።

በህዝብ የተመረጡት ሙርሲ እሥር ቤት ተወርውረው ፊልድ ማርሻል አዚዚ መለዮአቸውን አውልቀው የግብጽ ፕሬዚዳንት ለመሆን ሲነሱ ከዚያ የተላለፈው “የድጋፍ” ሥዕል ያስደነግጣል።

አከታትሎ ከአምስት መቶ በላይ የሚሆኑ የሞስሊም ወንድማማቾች “የሞት ፍርድ” በግብጽ ተፈረዶባቸዋል። ሰዎች ምንድነው የሚስቡት?

ከሚካኤል ጎርባቾቭ እና ከባሪስ ዬልሲን ከሶቪየትም መፈረካከስ መበተን ወዲህ ቪላዲሚር ፑቲን መጥተው „ጸጥታና ሰላምን የደስታን ዘመን የሩሲያ ታላቅነትን አድሳለሁ“ ብለው እንደተነሱ – ይህ አዲስ አይደለም ብዙዎቻችን ቀደም ሲል ሰምተናል።

ታይፔን ኤርድዋን በኢስታንቡል የከተማው ከንቲባ በነበሩበት ዘመን ከተማውን ከወንበዴዎችና ከቀማኞች እጽድተዋል፣ የወሃ ቧንቧ ዘርግተዋል ደስ ሲለው የሚበራውንና የሚጠፋውን የከተማውን መብራት ገመዱን አድሰው ሰውን ከማታ ጨለማ አውጥተዋል።
የሆቴል እና የቡና ቤት ባለቤቶች ነጋዴና ተማሪዎች…ሐኪምና ወላጆች ሁሉም በሰውዬው ሥራ -ቱርኮቹ እንደሚሉት ተደስተዋል።

በአስቸጋሪ ዘመን በመጥፎና መከራ ጊዜ ሰዎች አንድ መሪ ጠንካራ ክንድ ያለው መሪ ቢመጣላቸው ይፈልጋሉ። ይመኛሉ። እንዲመጣላቸውም ይጸልያሉ።

በጥንታዊት ግሪክ የጦር ስልት የሚቀይስ ቀይሶም ሠራዊቱን የሚመራ አንድ „ቆራጥ የጦር መሪ ጀግና:- ፊታውራሪ“ ፈልገው ይሾማሉ። እሱም ሳያስቡት ተገለባብጦባቸው በአንድ ሌሊት ተቀይሮ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ አናታቸው ላይ ሊጨፍርም ይችላል።
ይህን ከአዩ ደግሞ እሱን ያኔ እነሱ አይለቁትም።

ሮምና ሮማውያን „በየት መንገድ“ እንደሚኬድ፣ ችግርም እንዴት እንደሚፈታ፣ ከመከራ የሚያወጣቸው ሰው… ለሠራዊቱም ለሕዝቡም „መንገድ የሚያሳይ መሪ“ እነሱ „ዲክታተር“ ይሉታል (የጊዜ ገደብ ሰጥተው) ከአገኙ እሱን ሰይመው እሱን ይከተሉታል። ሳት ቢል ከመንገዱ ወለም ዘለም ከአለ ዩሊየስ ሴዛርን እንዳደረጉት አጋድመው ያርዱታል። እሱም እነኔሮና ሌሎቹ ቄሣሮቹ እንዳደረጉት አልሰማ ብለው „ያፈነገጡትን ይዞ ይፈጃቸዋል!“

የነገሥታቶችስ ሥራ እንዴት ነው?
እነሱ “በቅባ ቅዱስ” ይጨርሱታል።


ቤኒቶ ሞሰሊኒ በ1925 አጋማሽ ላይ „ዱቼ“ „መሪ „ የሚለውን ሹመት እሱ እራሱ መርጦ አናቱ ላይ ደፍቶአል። እሱን አይቶ አዶልፍ ሒትለር „ደር ፊውረር“ ያው መሪአችን ብለው ተከታዮቹ እንዲጠሩት ትዕዛዙን አስተላልፎአል። „መለኮታዊነቱን“ እየዘላበዱ እንዳያበላሹበት አብሮ አደጎቹን ከአጠገቡ ተራ በተራ ጠራርጎ ገድሎአቸዋል።
የጆርጂያው ተወላጅ የሩሲያ ኮሚኒስት ፓርቲው መሪ – እሱም ጓደኞቹንና አብሮ አደጎቹን ከአገጠገቡ በጽዳት ዘመቻ ቀስ በቀስ ከጠራረገና ከጨረሰ ወዲህ „…አባት! የአገር ሁሉ አባት!“ የሚባለውን ቅጽል ስም ትከሻው ላይ ለጥፎ ሁሉንም ጭጭ አድርጎአል። የኪዩባው ካስትሮ „ማክሲሞ ሊደር:- ታላቁ መሪ“ የሚለውን አጠራር መርጠዋል። ሳዳም ሁሴን „ተተኪ የሌለው መሪ“ እራሱን ሲያሰኝ „ወንድማዊ መሪ“ የሚለውን ጥሪ ኮነሬል ሞአመር ጋዳፊ መርጦ ለእራሱ ብቻ አድርጎአል።

ቆይተውም ኮነሬል ጋዳፊ ጥቂት የአፍሪካ „ንጉሦችን ከጋና እና ቤኒን ሰብስበው እራሳቸውን „ንጉሠ ነገሥት „ ብለው ሹመው የአፍሪካን መሪዎች ለእነዚያ አዳዲስ ማርቼዲስ ገዝተው የሚሸልሙት ሰዎች አዲስ አበባ ሲገቡ „…ንጉሣችሁ ሲመጣ እንዴት አይሮፕላን ጣቢያ ድረስ መጥታችሁ አትቀበሉም „ ብለው ተቆጥተዋቸዋል።
ኪም ኢል ጆንግ የኮሪያው „የበላይ መሪ“ የሚለውን ቃል ስም እና ዝና ክብርና ወግ ለብቻው ጨብጦ ይዞአል። ልጁም (አልጋ ወራሹም) ተመሳሳይ ጥሪ ወደፊት ይኖረዋል።

ግጥም ገጣሚዎች፣ ሞራ ገላጮች፣ ትንቢት ተናጋሪዎች ለሒትለርም ለሞሰለኒም ለሳዳም ሁሴን ለቢንላዲንም „….የእግዚአብሔር ስጦታ“ የሚለውን ሐረግ ፈልገው በዘመናቸው ሰጥተው ሰው እንዲያምንበት አድርገዋል።

በኢትዮጵያ አንዱ ዘፋኝ “አቤት ቅንድቡ…” ብሎ ሰውን አስጨፍሮአል። “ክቡር ሊቀ- መንበር አማራጭ የሌለው መሪ ” የሚለው ቃል “ከቀዳማዊት” ጋር አብሮ በአለፉት ዘመናት ከደርግ ዘመን ጊዜ ጀምሮ ተሰምቶአል።

አብዛኛዎቹ ይህን የሚሉትና ሰው እንዲያምነው ለማድረግ ጥረት የሚያደርጉ ክፍሎች የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ክፍል “ካድሬዎች” ናቸው።
የሚገርመው ሰዎች ሰዎችን አሳዶ የሚፈጅ ሰው -እንደ ሂትለርና ሞሰለኒ እንደ ስታሊንና እንደ… ያሉትን ሰዎች በጭፍን ተከትለው (በሰሜን ኮሪያ መሪው ሲሞት የግድ ይለቀሳል) እነዚህን ሰዎች„….የሚወዱአቸው“ በምን ምክንያት ነው? …ለምንድነው ጠንካራ ክንድ ለአለው ጨካኝ ሊሆን ይችላል ወይም… አስቸጋሪ ሰው “ሕዝቡ ጭፍን ” ድጋፉን የሚሰጠው?

„መሪን መውደድ“ ወይም መከተል ጊዜያዊ,፣ ነገ ንፋስ የሚመታው አቋም ነው? ወይስ ቋሚ ነገር? ለምንድነው ሰዎች በአንድ ዘመን አንድን “አደገኛ ሰው” የሚከተሉት በሌላ ጊዜ እሱን “እንደማያዉቁት ሰው” የሚክዱት?
ይህ ደግሞ ወደ ባለግርማ ሞገሱ ወደ „ካርስማቲክ መሪ“ አመጣጥና ውድቀት ምርምር ይወስደናል። ይህቺ ዓለም ሁሌ አዳዲስ ነገር አምጥታ ታሰደነግጣለች። ወይስ በእኛ ላይ ለመቀለድ ትደግማለች?

ምርጫ – አንድን መሪን ለተወሰነ ጊዜ ብቻ መምረጥ፣ እሱ ደግሞ ምንድነው?

The sun

 

 

 

……

logo-circ-reg

—-

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

Advertisements

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s