አባይ :- ኢትዮጵያና ግብጽ

አባይ :- ኢትዮጵያና ግብጽ

BlueNile

ንድ መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ የሚፈሱትን ወንዞች ሌሎች የጎረቤት አገር ከመድረሳቸው በፊት መገደብ ይችላል ? ወይስ አይችልም ? በሚል አርዕስቱ ሥር „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ የተባለው የደቡብ ጀርመኑ ዕለታዊ ጋዜጣ አንድ ሙሉ ገጹን ለዚሁ ወደፊት ዓለምን ሳያበጣብጥ አይቀርም ተብሎ ለሚገመተው ጉዳይ ጊዜውን ወስዶ ቅጠሉን ለግሶ የሚከተለውን አስተያየት አምዱ ላይ አሥፍሮአል።
ሌሎቹ የአፍሪካና የሰሜን አሜሪካ ጋዜጣዎች ስለ አፍሪካ ምን እንደጻፉ መለስ ብለን ዝርዝር ሁኔታ ውስጥ ሳንገባ ይህኛውን አርዕስት ብቻ ለመመልከት ወስነናል።
ጉዳዩ አሳሳቢና ቅድሚያ የሚሰጠው ነው።
መጪው ጦርነት እንደ ዘጠናዎቹ ዓ.ም “በዘርና በጎሣ….በብሔር/ብሔረሰብ” ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ጠበብቶች ተስማምተው እዚህ እንደሚሉት መጪው ጦርነት በሕይወት ጥያቄ ላይ ያተኮረ ነው።


… ምን እንብላ? ሰዎች ይላሉ።

ምን እንጠጣ?

ምን እንልበስ?

ማን ውጋታችንን ያስታግስ?

ምን እንሥራ?

የሥራ ዕድልና ትምህርት ጡረታና አንገት ማስገቢያ መጠለያ ቤት፣…የሚላስ የሚቀመስ…

የሚሉ ተጨባጭ የሰው ልጆች ጩኸቶች ናቸው።

ያኛው የመጀመሪያው ግጭት ኢትዮጵያንም ያበጣበጠው „የዘሩ ጉዳይ“ እንዲያው „የጠገቡ ልጆች“ ከመሬት ተነስተው አብሮ ለዘመናት ተጋበተውና ተካልሰው በመልካም ጉርብትና እና በአበልጅነት የሚኖሩትን ሰዎችና የተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮችን „ሆን ብሎ አጋጭቶ“ ሥልጣን ለይ፣ ጠበብቶች አሁን ደርሰውበት እዚህ እንደሚሉት “ሥልጣን ላይ ለመውጣት የሚያነሱት የሚጠቀሙበት መሰላልላና አወናባጅ ዘዴና ብልሃት ነው።”
ለዚህ ኤርትራ ጥሩ ምሳሌ ናት። ምንተገኘ አሁን እሷ ተገንጥላ? በመጨረሻውስ የት ተደረሰ? ማን ተጠቀመ?


ይህኛው አሁን „ሳይቀር ይመጣል“ የሚሉት ግጭትና ጦርነት በሞትና በሽረት በመኖር በአለ- መኖር በሕይወትና በመከራ ላይ የተመሠረተ ነው።


ሰዎች በአፍሪካ እንደ ሌላው ሕዝብ በልተው ጠግበው ማደር ይፈልጋሉ። የሚጠጣ ንጹህ ወሃ የሚለበስ ልብስ እንደሌላው ሕዝብ እነሱም…ይሻሉ። በተለይ ወጣቱ ትውልድ እንደ ወላጆቹ በቀላሉ ተታሎ ዝም ብሎ የሚገዛ-እነሱ እንደሚሉት- አይደለም።

ከዚህ አንጻር ሲታይ የወሃና የዳቦ….የልብስና የመድሓኒት የቤትና…. ጥያቄዎች የተቀበሩ ፈንጅ ቦንቦች ናቸው።
አፍሪካ ደግሞ በተለይ መሪዎቹ ለነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ሳትሰጥ እንደ አለፉት ዘመናት ነገሮችን ሁሉ ሸፋፍና እና አድበስብሳ ለማለፍ ከሞከረች/ከሞከሩ – ሌሎች ቦታዎች ተጽፎ አንደሚነበበው- ድብልቅልቁ አንድ ቀን መውጣቱ የማይቀር ነገር ነው።
የሚፈልሱትን ስደተኞቹን አይተው ረሃብተኛውን ቆጥረው …ትርምሱ ተጀምሮአል በርካታ ጋዜጣዎች ወደ ማለቱ ተሸጋግረዋል። በተለይ በወሃ አጠቃቀም ጉዳይ ላይ ከአልተነጋገሩ ከአልተደማመጡ መፍትሔም በጋራ (ከአገርም ሰው ከጎረቤትም ጋር) ቁጭ ብለው ከአልተለሙ መተናነቅ ጋዜጣው እንደሚለው የማይቀር ነገር ነው።
አብዛኛው ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የሰው ልጆች ዘር ሁሉ ቢቆጠሩ የሚኖሩት በወሃ ዳር ከእሱም በሚገኘው የእርሻ ምርት ነው።

“ሰዎች ከአልተስማሙ በወሃ ጥያቄ ጦርነት መታወጁ የማይቀር ነው” የሚለው የጀርመኑ ጋዜጣ በደቡብ አፍሪካና በሊሶቶ በኖቤል ሽልማት ተሸላሚው በኔልሰን ማንዴላ አንዴ በታወጀው የክተት አዋጅ ታሪክ (ስንቱ ያኔ ይህን ዜና እንደሰማ አይታወቅም) በእሱ ይጀምራል።

ደቡብ አፍሪካን የሚያጠጡ ጅረቶች የሚፈሱት ከሊሶቶ ተራራ የሚወርዱ ንጽህ ወሃ ናቸው። አንድ ቀን ሊሶቶ ወሃዬን እንደፈለኩት አደርጋለሁ ብላ የማንዴላን መንግሥት ለማሸበር አንድ ፕላን ጋዜጣው እንዳለው አውጥታለች። ይህም የሰላም ኖቤል ሽልማት አሸናፊውን ማንዴላን አስደንግጦ „…ወሃውን ልቀቂ አለበለዚያ የክተት ጦር ይከተላል“ የሚል ማስጠንቀቂያን ያስነሳል። በደቡብ አፍሪካ የተከበበቺው ሊሶቶ ከጀመረቺው ሓሳብ እራሱዋን ቶሎ ብላ ታርቃለች።

እንደዚያው ለኢትዮጵያም ከግብጽ አንድ ቀን ማስጠንቀቂያ መምጣቱ የማይቀር ነገር ነው ብሎ ቪኪሊክስ ላይ አንዴ የተነበበውን ሚሥጢር ጋዜጣው ያነሳል። „…ኢትዮጵያን እንመታለን!“ያሉትን ዛቻ መልሶ ጋዜጣው ያስታውሳል። አሁን ብዙ ቦታ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱዳን „በድብቅ መሬት ሸለመ /ሸጠ „ የሚባሉ ዜናዎችን በምናነብበት ሰዓት „ሱድ ዶች ሳይቱንግ “ የተባለው የጀርመኑ ጋዜጣ „የሱዳን መንግሥት ለግብጽ የጦር አይሮፕላኖች ማረፊያ መሬት -ያውም የኢትዮጵያ ድንበር አጠገብ- ሰጠች“ የሚለውን አረፍተ ነገር ይዞልን ብቅ ብሎአል።

የአባይ ወንዝ የሚነሳባቸውና የሚያቋርጣቸው አገሮች ብዙ ናቸው። ብሩንዲና ኬንያ ሩዋንዳና ሁለቱ ሱዳኖች ታንዛኒያና ኡጋንዳ በትንሴም ቢሆን ከኢትዮጵያ የተገነጠለቺው ኤርትራና እራሱዋ ትልቁዋ የጥቁር አባይ ወንዝ አቅራቢ ኢትዮጵያ እነዚህ ሁሉ ናቸው።

Nilemap


ግብጽ በጦር አይሮፕላኖቹዋ ተነሳታ ልትደባደብና ልትማታ የፈለገችው አገር ሌሎቹን ሳይሆን ኢትዮጵያን ያውም ድፍን ኢትዮጵያን ሳይሆን ከሱዳን የማይርቀውን የወሃ ግድብ ነው። ለግብጽ የጦር አይሮፕላን ማረፊያ ሱዳን ሰጠች የተባለውም መሬት ከዚያ ቦታ የማይርቅ ነው።

ሕጉ- የዓለም አቀፍ ሕጉ የአባይን ወሃ ለመጠቀም የሚፈቅደው ለማን ነው? ለግብጽ ወይስ ለኢትዮጵያ? መነጋገር የለም እንጂ መነጋገር ቢኖር መመካከር የለም እንጅ መመካከር ቢኖር እዚህ ጀርመን አገር ሰው የሚጠቀመውና የሚገለገልበት ወሃ ቢያንስ ከአምስት ጊዜ በላይ ተመልሶና ተጣርቶ በቧንቧ የሚመጣ ወሃ ነው።

ወሃ “ቆሻሻ”ተብሎ አንዴ የተጠቀምነው ወሃ ቢሆን እንኳን አይደፋም። ወሃን እንዲጣራና ተመልሶ እንደገና እንድንጠቀምበት ንጹህ ወሃው በቧንቧ እቤት ድረስ ሰተት ብሎ እንደመጣው ሁሉ በተማሳሳይ ዘዴ ተመልሶ በቧንቧ ያ ወሃ አንዲት ጠብታ ደጃፍ መሬት ላይ ሳትወድቅና ሳትደፋ ወደ ጥራት ገንዳው በቶቦ እዚያ እንዲደርስ ይላካል።

ነገሩ አጸያፊ ነገር ይመስላል። አክ የተባለበትንና የተተፋበትን ቆሻሻ ወኃን ወይም ደግሞ የሽንት ቤት መጸዳጃ ውሃን ሺህ ጊዜ ተጣርቶ ተመልሶ ቢመጣ እሱን እንደገና ማን ይጠቀመዋል? …ይዘገንናል።

ሳይንሱ ግን ሌላ ነው።1
የአባይን ውሃ የምድቴረኒያን ባህር ፈሶ ከመግባቱ በፊት አሥር ጊዜ መልሶ መላልሶ በኢትዮጵያም በሱዳንም በግብጽም አገር መጠቀም ይቻላል። ጋዜጣው ስለዚህ እንደዚህ ዓይነቱ የአጠቃቀም ዘዴ አያነሳም። ጋዜጣው በአጠቃላይ ያተኮረው በዓለም ሕግ መሠረት -በ1997 እአእ የወጣ ግልጽ ያልሆነ በሠላሣ መንግሥታት ብቻ የተደገፈ የተባበሩት መንግሥታት ደንብ አለ- በዚያ መሰረት የኢትዮጵያና የግብጽ መጪው ውዝግብ የት ያደርሳል ?ብሎ ይጠይቃል። እግረ መንገዱንም ስለ ኮንጎ ወንዝ ያነሳል። እዚያም የጎረቤት አገሮች በጋራ አንድ ግድብ ገድበው የኤሌትሪክ መብራት ኃይል አመንጨተው በጋራ ለመጠቀም እንደፈለጉም ይጠቅሳል። በተጋሊጦሹ የኮንጎ መንግሥት ይህን ሓሳብ በጥርጣሬ ዓይን ያየዋል ብሎ ዘገባውን ጸሓፊው ይዘጋል። የዞረበት ዓለም!

ትላንት ለጥራት የተላከው ወሃ ነገውን ተጣርቶ ለመጠጥ ወይም ለወጥ ሥራ በሁለተኛው ቀን አይቀርብም። የተጣራው ውሃ በክረምት ከወረደው ዝናብና ከበረዶ ወሃ ጋር ተደባልቆ መሬት ውስጥ ከተቀበረውም ንጸህ ወሃ ጋር ተቀላቆሎ ከአሥር አመትበ ሁዋላ በደንብ ጸድቶ አገልግሎትለላ ይውላል።

እራሱን የቻለ ሳይንስና ገንዘብ ጠሚያመጣ ሐብት ነው። ወሃ ለአወቀበት ሕዝብ አይደፋም። ጅረትም ዝም ብሎ አይፈስም።

 

……

logo-circ-reg

—-

ለ አእምሮ ሚያዝያ 2006 / April 2014 / እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 08

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s