የአድዋ ድል 118ኛ ዓመት
ዛሬ በየካቲት 23፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 1888 ዓ.ም. ከጠዋቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአሥራ አንድ ሰዓት ላይ የአድዋ ጦርነት ሲጀመር 118 ዓመት ይሆነዋል።*1
የአድዋን ድል 118ኛ ዓመት ለማስታወስ ስለ ዳግማዊ ምኒልክ ና የአድዋ ገድል :-
_
ጀግንነትና የአዋቂ ሰው ሥራ ታሪክ
የዘመናዊ ፖለቲካ አሠራር አጀማማር በኢትዮጵያ
*
ዜናው ተናፍሶ ወሬው ዓለምን አዳርሶ ጥቁሩንም ነጩንም ቀዩንም ፍጡር ከዚያም ራቅ ብለው የሚኖሩትንም ቢጫውንም ሕዝብ ያኔ ከነበሩት ከእነጌቶቻቸው ያስደነገጠው አንድ ነገር ቢኖር አደዋ ነው። *2
ትንሽ ቆይቶም ዜናው በቅኝ ግዛት መዳፍ ሥር ነጻነታቸውን ተገፈው የሚኖሩትን ያኔ „ባሪያዎች“ ተብለው የተናቁትን ሕዝቦች የልብ ልብ ሰጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስደሰተው በሁዋላም እንደምናነበው የታሪክ ጸሓፊዎችንም በብዙ ቦታ በጣም ያስገረመው የአደዋ ጦርነት፣ የተጀመረው በየካቲት 23 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 1888 ዓ.ም. ከጠዋቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአሥራ አንድ ሰዓት ላይ ነው። በዚህ በትክክል በስንት ሰዓት በሚለው ጥያቄ ላይ የተለያዩ ግምቶችና ማስረጃዎች -ከተለያዩ ሰዎች ይቀርባሉ።
በአንድ በኩል …ጦርና ጋሻ አንካሴና ጎራዴ፣ውጅግራ ጠበንጃና ምንሽር የያዙ ብሎኮና ነጠላ በርኖስና ካባ የደረቡ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች ተሰልፈዋል። በሌላ በኩል …ይህን ያህል ሺህ ወታደሮች መድፍና መትረየስ ቦንብና ዘመናዊ ጠበንጃ ሽጉጥና ሴንጢ ይዘው ታጥቀው በጥይት ሊቆሉአቸው መለዮ ኮፊያቸውን አድርገው ተደርድረው መሽገው ቆመዋል ።
የቀረውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ….(እንደገና የታተመ)
*1 – እአአ ማርች 1 ቀን 1896 (1st of March 1896) ተዘግቦ እናገኛለን!
*2 When Ethiopia Stunned the World
Book Review: The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire
_