ኢትዮጵያ የማን ናት? አሁንም እንደገና ! እንደገና !

ኢትዮጵያ የማን ናት?

(ካለፈው የቀጠለ)

ጥንት

ancient -Ethiopian

____

ሁለት ወገኖች እያለን። ለአንደኛው „ኢትዮጵያ“ የግል ሐብቱ ናት። እንደምናየው እሱም እንደፈለገው በቃላትም በገንዘብም እንደ ግል ንብረቱ „…ይሸጣታል። ይለውጣታል።“

ለሁለተኛው -እሱ ስለ ከዳት- ብትኖር ብትጠፋም እንደምናነበው ቅንጣት ያህል እንኳን ግድ የለውም።

እንደ ምንም ብሎ በዚያም በዚህም አድረጎ ድል አድረጎ ቤተ-መንግሥት ለገባው ሰው ሁሉ ይህች አገር እዚያም ምድር ላይ የሚኖር ሰው ሁሉ „የግል“ ሐብቱ ነውና ቢፈልግ ከመሬቱ ሊነቅለው ይችላል። ሊያባረውም።ሊያስረውም ። ሊቀጣውና ተደጋግሞ በተለያዩ ዘመናት እንደታየው ሊገድለውም ይችላል።

ደርግ እንደዚህ አድርጎ ነው በግዛት ዘመኑ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ያኔ የተመለከተው።

እህአዴግ ሻብዕያና ለጥቂት ጊዜያቶች አብሮ ከሁለቱ ጋር ለሠራው ኦነግ – ድል አድራጊ እነሱ በዘመናቸው ስለነበሩ- „ሁሉም ነገር“ ጊዜውም ዘመኑም ንብረቱም የኛ ነው ብለው የመጀመሪያው አመታት ላይ እነሱ እራሳቸው እንደጻፉት ቆይተውም እስከመተናነቅ የደረሱት ።

እንዲያውም „ተራው ከእንግዲህ የእኛ ነው!“ የሚለውን ቃል አብረው ለቀው „አርፋችሁ ተቀመጡ አለበለዚያ…“ የሚለውን ማስፈራሪያ አክለውበት በግዛታቸው የሚገኙትን ኃይሎች ጸጥ ለጥ ያደረጉት።

ድሮ

imperial Ethiopia

1

ቀደም ሲል እንደምናውቀው „እኛ ኢትዮጵያዊ አይደለንም“ የሚለውን ቅስቀሳም አካሂደው አባሎችም ደጋፊዎችም በየአለበት እነሱ ሰብሰበዋል።

በዘመኑ ተጽፎ እንደተነበበው „…የትግራይ ትግርኛ መንግሥት“ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ „የኦሮሞ ሪፓብሊክ“ ደግሞ እነደዚሁ ከኢትዮጵያ ተገንጥላ/ተገንጥለው በዚያ አካባቢ እነዚህ ድርጅቶች ለማቋቋም አቅደው አንደነበር በጽሑፍ ላይ ቀርቦአል በየአለበት -ምሥጢር ለማንም አይደለም ተነቦአል።

ለአረቡና ለቱርኩ ለሕንዱና ለቻይናው በሦስተኛ ደረጃ …ማንም ከየት መጥቶ የእርሻ መሬቱዋን በትንሽ ገንዘብ ለሚመጡት አርባና ሃምሳ ስድሳ አመታት …አልፎም ያሄዳል የሚገዛት ርካሽ አገር ናት።

ዛሬ መሬቱዋን ነገ ብሔራዊ ሕልውናዋን …ከነገ ወዲያ ደግሞ ሕዝቡዋን እንገዛለን ልንገዛ እንችላለን ባዮች ጥቂት አይደሉም።

አንግዲህ ይህች የፈረደባት ኢትዮጵያ ለመሆኑ ዛሬ የማን ናት?

2

እናት አገርን መክዳት አዲስ ነገር አይደለም። የትም ቦታ ያለ እና የሚታይ ነገር ነው። ቁጥራቸው ብዙ ሳይሆን ይህን የሚያደርጉ እንደዚህ የሚያስቡ ሰዎች በታሪክ ላይ ብዙ ቦታ ተደጋግሞ ታይቶአል። ግን ደግሞ በጣም ጥቂት ናቸው።

እንደ ኢትዮጵያ ግን ቅጥ ያጣ ቦታና አገር የለም።

ጌጥ ሁኖ አንዱ ወገን ሌላውን ለመብለጥ የማይልውና የማያደርግው ነገር የለም።

„ተማሩ“ ከሚባሉት ሰዎች መካከል ቁጥራቸው „ከፍ“ ያለ ወገን በእናት አገሩ በኢትዮጵያ ላይ አድሞ እሱ የሚሰነዝረውን አስተያየቱን ማዳመጡ የትም ያልታየ የትም ያልተሰማ በጣም የሚገርም አዲስ ነገር ነው።

በታሪካችን ጦር መዘው ከጠላት ጋር ቆመው ይህቺን አገር የወጉ ሰዎች አሉ። ይህም ታሪክ ብዙ ቦታ ተመዝግቦ ይገኛል። መጥላት ብቻ ሳይሆን እንድትጠፋም የሚፈልጉ ሰዎችን አገሪቱ እንደሌሎቹ -ይህ የትም ያለ ነው- አፍርታለች። እንደነሱ ያሉትንም ብዙ አካባቢዎች እናያለን።

„የምኒልክ ኢትዮጵያ ትሙት… „ ብለው እኛ ጋ እንደሚፈርሙት ዓይነት ሰዎች ሌላም አካባቢም ታሪክ ላይ እንደአነበብነው የትም በቅለዋል።

የኢትዮጵያው ግን ይብሳል። ብሶበታል ከሁሉም ይበልጣል።

ለምን እንደዚህ ሆኑ?

ለምን እነደዚህ ጨከኑ? ለምን አገራቸውን ጠሉ? ባለማወቅ ይሆን ወይስ አውቀው ነው ይህን የሚያደርጉት?ማንን ለመጥቀም?ማንን ለመጉዳት?

ፕሬዚዳንቱዋ የነበሩት ሰው ከእሳቸው አፍ የሚሰማው ያስገርማል። አገረ ገዢዎቹ የሚሉትን ስንሰማ ያስደነግጣል።

ዛሬ

post-ethiopia_map

3

ኢትዮጵያ የማን ናት? ብሎ መጠየቅ አሜሪካን የማን ናት? ብሎ እንደመጠየቅ ነው። …ፈረንሣይስ የማን ናት? ታላቁዋ ብርታኒያስ? ቻይናስ? ኬንያስ? ሕንድስ የማን ናት? ብሎም ጠይቆ መልስ እንደመፈለግ ዓይነት ነው።

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያኖች አገር ናት። ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምን ሰው ሁሉ አገር ናት። መልሱ የዚህን ያህል ቀላል ነው።

አሜሪካ አገር ሄደው የሚወልዱትንም ዘመዶቻችን መረዳት የምንችለው ይህን ስንገነዘብ ነው። እዚያ የተወለደ ልጅ እዚያ ዜግነቱን የተቀበለ ሰው እሱ „ ሙሉ አሜሪካዊ ሙሉ የአሜሪካ ዜጋ ነው።“

ይህ ልጅ ወደፊት ሊመረጥም ሊመርጥም ከፍተኛ የኃላፊነትም ደረጃ ላይ -ቀለሙ ዘሩ ሓብቱ ጾታው ሳይታይ- እዚያ ስለተወለደ መሰላሉ ላይ ሊወጣም ይችላል።

ኢትዮጵያ ውስጥም የተወለዱ አርመኖችና ጣሊያኖች ግሪኮችና አረቦች ሱዳንና ግብጾች ሕንዶችና…( አሁን ደግሞ ቻይናዎች(?)ተጨምረውበታል) እነዚህ ሁሉ የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ናቸው።

ማለት በሕግ በታወቀው ግዛቱዋ ያኔም /አሁንም የተወለደ ሰው ሁሉ (የዛሬውን አናውቅም)የአገሪቱ ዜጋ ነው። ናቸው።

ግን ደግሞ በዚያው መጠን „እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም „ የሚለውን ሰው -ይህን ለማለት መብቱ ነው- በግዳጅ ኢትዮጵያዊ ማድረግ አይቻልም።

ይህ ከሆነ ደግሞ „ኢትዮጵያዊነቱን“ ከማይቀበል ሰው ጋር ጥዋት ማታ መነታረኩ -ባልና ሚስት እሰከ አልሆኑ ድረስ- ከንቱ ነው።

„እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም „ ብሎ „በኢትዮጵያዊነቱ ለመደራደር…“ ከሚፈልግ ሰውና ድርጅት/ድርጅቶች ጋር ምን ማድርግ ይቻላል? ስለምን መደራደር እነሱ እንደሚሉት ይቻላል? ማን በማን ስምና ሌጋሲ ድርድሩን ሊያካሄድ ይችላል? ምን ላይ ተመስርቶስ መነጋገር ይቻላል?

4

እንደዚህ ዓይነቱን „ችግር“ ሌላው ዓለም በሌላ ብልሃት ነው የፈታው።

አንድ አገር አንድ መንግሥት አንድ መሬት አንድ ክልል የአንድ ድርጅት የአንድ ቡድን ወይም ደግሞ የአንድ የታጠቀ ወይም ያልታጠቀ ኃይል ንብረትና ሓብት አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ይህ ሆኖአል። ለምሳሌ ኤርትራ።

አንድ አገር አንድ ሕዝብ የአንድ ቡድን ወይም የአንድ ድርጅት “የግል ሓብት” ከሆነ ሁሉም እንደ ቅርጫ ለመቀራመት የሚነሳበት የሽፍቶች መፋለሚያ ሜዳና ጫካ ሆነ ማለት ነው። ይህ በኢትዮጵያ ይታያል።ይህም በአገራችን ሁኖአል።

በድፍን አፍሪካ አሁን የምናየውም ሥዕል ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው።

በግብጽ የጦር ሠራዊቱ በአፍጋኒስታን ታሊባኑ በኢራን አያቶላዎቹ በሱማሌ እያንዳንዳኑ ጎሣ በኮንጎ የታጠቀ ሽፍታ በቻድና በሴንትራል አፍሪካ ወይም ደግሞ በናይጄሪያ የሃይማኖት ሚሊሻ በሊቢያ በሱዳን አገራቸውና አካባቢው ወይም ሕዝቡ በጠቅላላው „የእኛ ነው“ ብለው እንደ ሓብታቸው የሚያዩ ክፍሎች እዚያ ተበራክተዋል። ማን መርቆ ሰጣቸው? ይህ የትም ቦታ በትክክሉ ተነስቶ ያልተመለሰ ጥያቄ ነው።

እንደዚህ ዓይነቱ ጥያቄ እንዳይነሳ እንዲያውም እንዳይታሰብ ጉልበተኞቹ – ሁኔታዎች እንደሚመሰክሩት ማገድ ይችሉበታል።

5

ደርግ ለአሥራ ሰባት አመት እንደዚህ ዓይነቱን አመለካከትና የአገዛዝ ሥልት ከድሬዎቹን „የለውጥ ሐዋሪያ“ ብሎ በሁሉም አቅጣጫ አሰማርቶ እሱ ለብቻው ቤተ-መንግሥት ገብቶ እግሩን ዘርግቶ እስከሚበተንበት ሰዓት ድረስ ማንም ሳይጠይቀው ቀልዶብን ሄዶአል።

ከዚያ በፊት ንጉሠ ነገሥቱ ከመሣፍንቶቹ ጋር የበላይነቱን ይዘው ጸጥ ለጥ አድርገው ገዝተዋል።

ሌሎቹ የመንግሥት ግልበጣ ሙከራ አድርገው ሳይሳካላቸው ተቀጭተው ቀርተዋል። ከዚያ ሁዋላ የመጣው ጊዜ ደግሞ እንደምናውቀው ለሁለት ና ሦስት ድርጅቶች አመችቶአል።

በምንም ዓይነት አንድ ቡድን (የታጠቀ ይሁን ያልታጠቀ) ለአንድ አገር ውስጣዊ ችግር እሱ እራሱ ብቻውን መፍትሔ አቅራቢ መፍትሔ ፈላጊ መፍትሔ ሰጪና ለመፍትሔውም ትክክለኛ ፍርድ ሰጪ እሱ ሊሆን አይችልም።

ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ተደርጎ በዓይናችን አይተናል።

እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ደግሞ በሦስት ነገሮች (ሌላው ዓለም በዚህ ነው የተገራው) ከእንግዲህ በሰላም እኛም እንደሌሎቹ ሕዝቦችና መንግሥታት እንኑር ከአልን መታገድ ይገባዋል።

አንደኛው በነጻ ምርጫና በሥልጣን ዘመን ላይ የጊዜ ገደብ በሕግ ሲጣልበት ብቻ ነው። ሁለተኛው በሥልጣን ክፍፍልና ሽንሸና እሱን በሚቆጣጠሩ ተቋሞች „ገዢው“ መደብ እጅና እግሩ በሕግ„ተተብትቦ“ እንደ ሌላው አገር ተከቦ ሲያዝ ብቻ ነው ።

ከሁሉም ሦስተኛው የሰበዓዊ መብቶች ተከብሮ ሰው ሁሉ „ገዢውም ሆነ ተገዢውም“ በሕግ ፊት አለ አድሎ እኩል ሁነው ሲቆሙም ብቻ ነው።

6

ኢትዮጵያ የማን ናት? የሚለው ጥያቄ ያኔ ኢትዮጵያ የእኛ ናት በሚለው በብዙ ሚሊዮን በሚቆጠሩ ዜጎቹዋ ይመለሳል። ይህ ደግሞ በምንም ዓይነት ኢትዮጵያ የጥቂት የተደራጁ ሰዎች የግል ሐብት አይደለችም የሚለውን አመለካከት ያጠናክራል።

የኢትዮጵያ ችግር የመጣው ይኸው ችግር ከአርባ አመት በላይ የሰነበተብን አሁንም ከዚያ ወጥተን ወደፊት እንደሌሎቹ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መራመድ ያልቻለነው ኤርትራ የተገነጠለቺው ሌላው ዛሬ ልገንጠል የሚለው ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች በአገሪቱ በአለመኖሩ ነው። አንድ ፍልስፍና ደግሞ አገራችን ገብቶ የትውልዱን አእምሮ ጨፍድዶ ይዞ እራሳቸውን በንጉሡ ዘመን ዲምክራሲ ዲሞክራሲ የሚሉትን ወጣቶች ዓይን -የሚታወቀውን ለመድገም- ጋርዶአል።

ነጻ -ፕሬስ እነደ ኬንያና ታንዛኒያ በኢትዮጵያ የማናየው በይፋ አንድን ድርጅት መቃወም ወይም መደግፍ የማያቻለው… የስታሊንና የማኦ ፍልስፋናዎች አገራችን በመግባታቸው ነው።

እነዚህ ትምህርቶች በሰሜን ኮሪያና በኪዩባ እንደ ንጉሠ-ነገሥቱ ዘመናት የቤተሰብ ዳይናስቲ ዓይናችን እያየ ተክለዋል። በቻይና እንደ የዱላ እሩጫ ቅብብል ሥልጣኑን ከአንዱ ቡድን ወደ ሌላው የሚያንከባልሉበት ሁኖአል።

አውሮፓን እንተውና ኬንያ ናይጄሪያ ደቡብ አፍሪካ …ኒዚያና ጋና… በዘር ሳይከፋፈሉ የዲሞክራሲውን አየር ተንፍሰው በሰላም የሚኖሩት እዚያ የሌን እና የስታሊን ብሔር /ብሔረሰብ እስከ መገንጠል…የሚለው ፍልስፍና እነሱ ጋ በአለመድረሱ ድርሽ በአለማለቱ ነው።africa-bevor-col-small

ኢትዮጵያ የማን ናት?የሚለውን ጥያቄ በትክክል የምንመልሰው ከስታሊን የአገርና የዘር ሽንሸና አመለካከትና አስተሳሰብ ስንወጣና ዓለምን በሌላ ዓይን ስንለመከት ብቻ ነው።

ምን ዓይነት አመለካከት?

አንድ ሰው አንድ ድምጽ በኢትዮጵያ ሲኖሩ ብቻ ነው።ፖለቲከኞቻችንም ሰው ፊት ቀርበው -ሌላው ዓለም እንደሚያደርገው- የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን አሳይተው ተወዳድረው ተናግረው አሳምነው ለተወሰነች አራት አመት ብቻ በትችት ታጅበው በተቋሞች ታጥረው ሽንጎ ውስጥ ተመርጠው ሲላወሱ ብቻ ነው።

እንግዲህ ያኔ ደግሞ ኢትዮጵያ የማንም ሳትሆን የዘጠና ሚሊዮኑ ኑዋሪዎቹዋ የጋራ ቤት የጋራ ሐብት የምትሆነው።ኤርትራም እንደዚሁ።

ከዚህ ውጭ በየጊዜው የዘርና የጎሣ የብሔር /ብሔረሰብ ጥያቄ እያነሱ ሰውን ማጋጨት በሕግና ወደፊት በታሪክ ፊት በሞራልም ያሰጠይቃል።

…ልዩ የሆነ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ አዲስ ጎማ„ ፈረንጆቹ አጉል የሆነ ግራ የሚያጋባ የሚያስቅ ፍልስፍና አንዳንድ ሰዎች ሰንዝረው መጫወት ሲቃጣቸው እነሱ የሚናገሩትን ነገር እንደገና ለመድገም-በዓለምም በኢትዮጵያም „…አዲስ የትም ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የሚሽከረከር ጎማ ለመፍጠር እንዲያው አትድከም“ ይላሉ። “ጊዜህን ወርቅማ ጊዜህን በሌላ ቁም ነገር ላይ እባክአውለው ” ልጆቻቸውን ይላሉ።

ነገ

?!

ከሣቴ ብርሃን

አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር-7

Advertisements

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s