ከ ታ ሪ ክ ሰ ነ ድ:-
ቀኃሥ ና ማርቲን ሉተር ኪንግ
ስድሣው አመተ ምህረት የእኩልነት ጥያቄ ዘመን ነበር። በ1969 (እ.አ.አ.) የሰብዓዊ መብት ታጋዩ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በዘረኞቹ “በነጭ ዘር በላይነት” በሚያምኑ ነፍስ ገዳዮች የተገደለበት ዓመትም ነበር።
የማርቲን ሉተር ኪንግ ጥያቄ “…የመገንጠል” ሳይሆን የነጮችና የጥቁር ዘሮች የእኩልነት ጥያቄ ነበር።
በዚያን ዘመን ለማስታወስ በአገራችን በኢትጵያ ወጣቱ ትውልድ በብዙዎቹ ዘንድ ያኔ ማንነቱ ምን እንደሆነ እንደአሁኑ ዘመን በግልጽ በአልታወቀው አይዶሎጂ ተሳከረው ከእኩልነት አልፎ የሚሄደውን “…የመገንጠል” ጥያቄም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ “ኢትዮጵያ የሚባል ነገር የለም ብለው” በስታሊን ስም ተነስተው አሁን ያለንበት ሁኔታ ውስጥ ሳያመዛዝኑ ከተውን ሄደዋል።
የዘረኝነት የፖለቲካ ጉዞና ተንኮል የገባቸው ቀ ኃ ሥ በማርቲን ሉተር ኪንግ መገደል ሃዘናቸውን ለመግለጽ ከመንገድ ወጥተው፣ ለጥቁር ህዝብና ትግል ወገናዊነታቸውን ለመግለጽ ወላጆቹንም ለማጽናናት፣ ፎቶውና ጋዜጣው ላይ የሰፈረው ዜና እንደሚያሳየው የአበባ ጉንጉን መቃብሩ ላይ አስቀምጠው መንገዳቸውን ቀጥለዋል።
ለአእምሮየጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6