ቤተ-ክርስቲያን ሲሸጥ ሲለወጥ!

ቤተ-ክርስቲያን ሲሸጥ ሲለወጥ!

መኑ ተቀይሮአል።

Lutherian-churchተቀርጾ አንድ ቀን በዜና መልክ በቴሌቭዠን የተላለፈው ፊልም ከአእምሮ በቀላሉ አይጠፋም። ያኔ የተጀመረውም ጉዞ በፈጣን እርምጃ አሁን ወደፊት ቀጥሎአል።

በጸሎት ሥነ-ስርዓት ነበር ያ መቅደስ ለመጨረሻ ጊዜ የተዘጋው።በርካታ ጋዜጠኞችም ታሪኩን አጅበውታል። ብዙዎቹ ደንግጠው አስተያታቸውን ሰጥተውበታል። አቴስቶቹ ምንም ነገር እንዳልሆነ በአጠገቡ አልፈዋል።

ከመዘጋቱ በፊት ቀሳውስቶቹ የእሁድ ጥዋት ተሰብሰበው እንደተለመደው የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል። ምዕመናን ሥጋ ወደሙ ለመጨረሻ ጊዜ ተቀብለዋል። መዝሙር ሁሉም አብረው ዘምረዋል።

ከዚያ በሁዋላ ተራ በተራ እና አንድ በአንድ ቀስ እያሉ የቤተ ክርሰተያኑን መስቀሎች ሥዕሎች መጽሓፍትና ውድ የስጦታ ዕቃዎች ዋንጫና የቄሶች ልብሶች ካባና የሻማ መስቀመጫዎችን እየተሸከሙ አውጥተው መኪና ላይ እየዘመሩ ጭነው ወደ ቤታቸው በሩን ዘግተው ተመልሰዋል።

እዚያ የቀረው የሕጻናት መጠመቂያ አሸንዳና አግዳሚ ወንበሮቹ ብቻ ናቸው።

በዚያን ቀን ሆነ በሌሎች የጸሎት ቀናት ያለፉት አመታት በተከታታይ አንድም ልጅ አልተጠመቀበትም።

ችግሩ ያለውም እዚያ ላይ ነው።

ወጣቱና ተተኪው ትውልድ እንደ አባቶቻቸውና እንደ እናቶታቸው ቤተክርስቲያን መሄድ ሄዶ መጸለይ እነሱ ከአቆሙ ጊዜው ረዘም ይላል።

ጸሎት ለእነሱ መንፈስን ማደስ ሳይሆን ግዳጅ ይመስላቸዋል።መጽሓፍ መድገም ስብከት መስማት የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ ንስሓ መግባት እነዚህ ሁሉ -በእነሱ ዓይን -ጊዜው ያለፈበትና ከዘመኑ ዕውቀትና ሥልጣኔ ጋርም አብሮ የማይሄዱ ነገሮች ናቸው ባይ ናቸው።

ከዚያም በላይ በሰበሰቡትና በአገኙት ዕውቀት „እግዚአብሔር የለም“ ከእነሱ መካከል የሚሉ ብዙ ናቸው።

ይህ ሁሉ አመለካከት ደግሞ በመጨረሻው ለቤተ ክርስቲያን እንደወላጆቻቸውና እንደ አያት ቅድመ አያቶቻቸው በተራቸው ይህን ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ የሚገባቸውን ኃላፊነት „እምቢ … ግብርም ለቤተ-ክርስቲያን አንከፍልም „ እነሱን ወደሚለው ውሳኔም ወስዶአቸዋል።

„ቤተ-ክርስቲያኑን የምናስተዳድርበት ገንዘብ ቢኖረን „አስተዳዳሪው ቄሱ እንዳሉት „…ይህኛውን ባልዘጋነውና ቢያንስ በአሉትና ከቀሩት ሰዎች ጋር አብረን ተሰብስበን አንድላይ በየሳምንቱ እያስቀደስን በቆየን ነበር….“ ብለዋል።

ከአሜሪካን አገር የመጡ አገር ጎብኚዎችና የሉተር ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን ተከታዮች ጀርመን አገር ሲመጡና የጀርመንን ምዕምናን ሲመለከቱ „….ለመሆኑ እምነቱ የት ደረሰ ?“ብለው ሁሌ ያገኙትን ሰው እዚህ ይጠይቃሉ።

በእርግጥ የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ኮሚኒስት መንግሥት ሃይማኖትንና ቤተ ክርስቲያንን አጥላልቶ ብዙዎቹን ተከታዮች አዳክሞ ቤተ ክርስቲያኑዋን በጉልበቱና በፕሮፓጋንዳው ኦና ለማድረግ ብዙ ጥረት አድርጎአል።

አሁን ግን ሰውን ሁሉ ግራ እያጋባ የመጣው በሰሜን ጀርመን ትላልቅ ከተማዎች እንደ በረሊንና እንደ ሓምቡርግ እንዲሁም በዝቅተኛው ሳክሶኒያ ማለት በአብዛኛው ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አማኞች መካከል እንደ ኮሚኒስቶቹ እዚህ መንግሥት ጫናውን በማያሳይበት አገር የምዕመናኑ ቁጥር ቀንሶ ቤተክርስቲያን እስከ መዝጋት ድረስ ያደረሰው ጉዳይ ምን እንደሆነ እሱን ለመረዳት ብዙ ሰው ግራ ተጋብቶታል።

በደቡቡ ጀርመን በካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ፈጽሞ እዚያ አካባቢ አይታይም። katholic-church

ካቶሊኮች ኃይለኛ ሥርዓትና የጠበቀ እምነት እንዳላቸው ይነገርላቸው። ወላጆችም ባህሉን ሥነሥርዓቱን ወጉን ትውፈቱን የመጽሓፍ ቅዱስ ጥናቱንና ሳምንታዊ ትምህርቱን ለልጆቻቸው ተቆጣጥረውና ጠብቀው ለእነሱ እንደተላለፈው እነሱም ማስተላለፉን-እዚህ እንደሚባለው- ይችሉበታል።

የሉተር ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን አማኞች ግን ይህን ኃላፊነት እንዳአልቻሉበት አሁን የተፈጠረው ክስተት ያሳያል።

በርካታ ቤተ-ክርስቲያኖች እዚህ ሰሜን ጀርመን መቅደሱ ኦና ሁኖ አሁን ለሽያጭ ቀርበዋል።

እኔ እራሴ የዛሬ ሃያ አምስት አመት በፊት ለዕረፍት ወደ ዝቅተኛው ሳክሶንያ ክፍለ-አገር ከጓደኞቼ ጋር በወረድኩበት ጊዜ ራት የት ልንበላ እንችላላለን? ብለን ጠይቀን የተሰጠን አድራሻ በር ላይ ስንደርሰ ተደናግጬ ያለሁበትንና የደረስንበትን ቦታና ቤት ቀና ብዬ አይቼ ዓይኔን ማመን ፈጽሞ አቅቶኝ ነበር።

ፈልገን እራት ለመብላት የደረስንበት ቤት አንድ ጥንታዊ ትልቅ ቤተክርስቲያን ነው። በሩን ከፍተን ስንገባ ለስላሳ ሙዚቃ ይሰማል። መቅደሱ ላይ ዱሮ ቄሱ የሚቀድስበትና ሥጋው ወደሙ ሰዎች የሚቀበሉበት ቦታ ወይም ሠርገኞች ቀለበት ተለዋውጠው የፈቃደኛነት ቃለቸውን የሚሰጡበት ሥፍራ ቢራውና ሌሎች መጠጦች የሚቀዱበት „ባንኮኒ“ ነው።

በመጽሓፍና በሻማ ፋንታ የአረቄ ጠርሙስና የምግብ ማዘዣ ደብተሮች የሲጋራ መተርኮሻ ትናንሽ ሳህኖች ሹካና ማንኪያ ተቀምጠዋል።

አሰላፊ ሠራተኛ ሴቶች ከግራና ከቀኝ ቱር ቱር እያሉ መጠጡንና ምግቡን ዱሮ አግዳሚ ወንበር በነበረበት አሁን ጠረጴዛና ወንበር ይዘው ሲጋራቸውን እያጤሱ ለሚጠብቁ ሰዎች ያቀርባሉ።

እምድር ቤቱ ሰለሞላ እኛን ወደላይ ወደ ሠገነቱ ቦታ እንዳለ አንደኛዋ ጠቁማን „ሂዱ ውጡ እኔ እመጣለሁ“ ብላ ሥራዋን ቀጠለች።

ምግባችንን አዘን ቢራችንን እና ወይናችንን ጠጥተን ማዕድቤቱ ለመሆኑ የትነው ብዬ ጠየኩ። እሱም ከመቅደሱ ጀርባ እንደሆነ ተነገረኝ። መጸዳጃ ቤቱም -ለወንድና ለሴት ዱሮም ቢሆን የነበረበት ቦታ እዚያው ቤተ-ክርስቲያኑ ምድር ቤት ውስጥ እንዳለ ተነገረኝ።

ይህ የዛሬ ሃያ አምስት አመት ታሪክ ነው።

አሁን ጊዜው ተቀይሮ የቀድሞ ቤተክርስቲያኖች የወጣቶች ዳንኪራ መራገጫ፣ የልብስና የመጽሓፍት ወይም ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ቤቶች ሁነዋል። አንዳንዴም የሙዚቃ መደገሻ ቤቶችእና የሥዕል ኤግዚቪዥን መድረኮችም ሁነው ያገለግላሉ።

አንዳንዶቹ ተሸጠው የግሪክና የራሸያ የሶሪያና የግብጽ ኦርቶዶክሶች ፣የፖላንድ ካቶሊኮች፣ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮችም ገንዘብ ከአላቸው የሚገዙት ሁነዋል። ይህ ብዙዎቹ ከሆነ አይቀር ሲጠየቁ የሚመኙት ነው።

ያለፈው አመት ደግሞ የሓምቡርጉን የእቫንጀሊስት ቤተክርስትያን ለመግዛት እንፈልጋለን ብለው የቀረቡት እንግዶች ሌሎች ሁነዋል።

„አል- ኑር“ የሚባል አንድ በሕግ የተመዘገበ የእስላም ሃይማኖት ተከታዮች ማህበር ይህን ሕንጻ ገዝቶ ወደ መስጊድ ለመቀየር ሓሳቡን ግልጽ ከአደረገ ወዲህ ኃይለኛ ክርክር ተነስቶ ደጋፊውንም ተቃዋሚውንም አነጋግሮ „…ለምን ይህ ይሆናል? ….ለምን መሆን የለበትም?“ ወደሚለው ጥያቄ ሻጮቹንም አማኞቹንም ሰውንም ሁሉ ወደዚያ ወስዶአቸዋል።

„…እንዴት መስቀልን በግማሽ ጨረቃ እንለውጣለን? እነዴትስ ዓናችን እያየ ወደዚያ ይለወጣል?“ አንዳዶቹ ሲሉ „…ከዳንኪራና ከመሸታ ቤት መስጊድ ቢሆን ይሻላል።“ የሚል መልስም ከአንዳንዶቹ እንደዚህ ሲባል ተሰምቶአል።

„…ዘመናዊሥልጣኔና አጉል የሃይማኖት ንቀት ይህን አምጥቶ ሜዳውን ለሞስሊሞቹ አመቻችቶ ሰጠ „ ብለው ሌሎቹ አማረው ተናግረዋል። „በምንም ዓይነት መሽጥ የለበትም።ሁለቱ ሃይማኖቶች ካቶሊክና ኢቫንጀሊስቶቹ አንድ ላይ ቆመው ይህን ነገር ማገድ አለባቸው። „ ብለው አንድንድ ቀሳውስቶች ተነስተዋል።

ግን የሁለቱ አንዴ ተለያይተው ይኖሩ የነበሩ ቤተ ክርስቲያኖች ስምምነት „አንድ ለመሆን“ ብዙ ጊዜ ይጠይቃል።

ይህ ሁሉ የሆነው „…ብዙ ቤተ-ክርስቲያኖች በስድሳውና በሰባው አመተ ምህረት አለ ፕላን በመሰራታቸው ነው …“የሚሉም ሰዎች ድምጽ ሓምቡርግ ላይ ተሰምቶአል።

ችግሩ ያለው እሱ ላይ ሳይሆን ብዙው ወጣት ትውልድ ከቤተ-ክርስቲያን በመራቁ ነው።

ወጣ ወረደ ገዢዋቹ የሞስሊም ማህበረሰብ „…ውስጡን አድሰን መስጊድ አድርገን እንሰግድበታለን“ብለዋል።

በአምስተረዳም ከተማ በሆላንድ ቤተ-ክረስቲያን የብስክሌት ማቆሚያም ሁኖአል።

ማርቲን ሉተር ይህ ቀን ይመጣል ብሎ እንቅስቃሴውን ሲጀምር ፈጽሞ አላሰበም ነበር።

እንደ መከፋፈል መጥፎ ነገር የለም። ክፉ ቀን ሲመጣ እነደ መጠጊያና መጠለያ እምነትና ተሰፋ የሚሰጥ ቤት የትም አይገኝም።

Ethiopian-church„…እስላሞቹ እነሱን የሚያሰባስብና አንድ የሚያደርጋቸው ጠንካራ ሃይመኖት አላቸው። እኛን ምዕራቦቹን ግን ምን የሚያሰባስበን ነገር አለ? ዋናው ጥያቄ „ አንዱ እንዳለው „እሱ ነው ብሎ“ ከእኔ ተሰናብቶአል።

ዕውነት አለው።

Advertisements

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s