ከታሪክ ሰነድ ፥ ጣይቱ ብልሂቷ (ደብዳቤ)

 

ከታሪክ ሰነድ ፥ ጣይቱ ብልሂቷ (ደብዳቤ)

የተላከ ከእቴጌ ጣይቱ ብረሃነ ዘኢትዮጵያ

(የላይኛው ሰነድ እንደገና ሲጻፍ )

የተላከ ከእቴጌ ጥይቱ ብረሃነ ዘኢትዮጵያ

ይድረስ ከማህበረ ዲር ሥልጣን ወደብረ ገነት ዘኢየሩሳሌም።

እንዴት ሰንብታችኀል። እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ።

እናንተ ብትስማሙ እርስ በርሳችሁ ብትፋቀሩ አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻልል እንጂ ትግሬ የብቻው ነው ሸዋ የብቻው ነው ቢገምድር ጎጃም የብቻው ነው እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ።

እኛስ በኢየሩሳሌም ነገር ይህን ያህል መድከማችን ያንን ያህል ብር ባንክ አግብተን የዚያን ወለድና አቤቱ የሚወጣውን ክራይ መስጠታችን እንዳትቸገሩ የሰው ፊት እንዳታዩ ያንን እየበላችሁ ለኛም የጌታችን ደም ከፈሰሰበት ላይ ዳዊት እብድትደግሙልን እንድታዝኑልን እናንተም ፩ ነታችሁን እንዲጸና ብለን ነው እንጅ ገንዘቡ ተርፎ ባገራችን በኢትዮጵያ ለምንሰጠው ሰው አጥተን አይደለም።አሁንም ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ እናንተም እርስ በእርሳቸሁ

ተፋቀሩ ለኛም ዳዊት ድገሙልን እዘኑልን ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሣቂያ ትሆናላችሁ።

አሁንም ይኸው እማሆይ ወለተ ተክሌ መቃብሬ ከዚያውይሁን ብላ መጥታለችና

አደራችሁን በምኑም በምኑም ነገር እንዳታስቀይሟት። እንግዲህ ሷ እንዲህ አደረጉኝ ብላ የላከብችን እንደሆን እናንተንም እጠላችኀለሁ።እኔንም እንዳስትቀይሙኝ።

29 ቀን 1900 ዓመት አዲስ አበባ ከተማ ተጻፈ

ንገሥት ጣይቱ፥ ጅግናዋ

ንገሥት ጣይቱ፥ ጅግናዋ

***

መልዕክቱ

በነገር አሁን ለተሳከረውና ለማይደማመጠው ትውልድ የተጻፈ ይመስላል

ደፊት „በባዕድ ፊት መሳቂያና መሳለቂያ“ እንደይሆኑም ምክርና ተግሣጽ ይኸው ደብዳቤ ይሰነዝራል።

የተለያዩና የተበጣበጡ የኢትዮጵያ ልጆችንም ያስጠነቅቃል።

፩ ነታችሁን አጽኑም …ይላል።

የተጻፈው ከመቶ አመት በፊት ነው። የተላከውም ከሺህ ሰምንት መቶ አመት በፊት ጅምሮ ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምሥራቅ በኢየሩሳሌም ለምስታተዳድረው ገዳም ኑዋሪዎች ነው።

„…እናንተ ብትስማሙ እርስ በእርሳችሁ ብትፋቀሩ አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻላል …“ የሚለው ደብዳቤው ላይ የሰፈረው የዓረፍተ ነገር አሰካክ የሐዋሪያው ጳውሎስን መልዕክት -አንድ አንባቢን ያስታውሳል።

ይህም እቴጌይቱ አርቀው የሚያስቡ የስው ልጆች ባህሪና የሰው ልጆች የተፈጥሮ ድክመት የት ላይ እንደሆነ አንዴትም መታረም እነደ አለበት ደህና አድረጎ የገባቸው መሆኑን ከደብዳቤው መልዕክት መገንዘብምይችላል።

እቴጌይቱ ከባለቤታቸው ከአጼ ምኒልክ ጋር ጥሩ የፖለቲካ ቀያሽ (ስታረተጂስት) መሆናቸው አደዋ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላም መስክ ላይ ደህና አድርገው በጊዜአቸው ማን መሆናቸውን አሳይተው አስመስክረዋል። ።

እቴጌ ጣይቱ እንደ አጼ ምኒልክ-ብዙዎቹ እንደሚሉት-የሰው ምክር አዳምጠውም መርምረው አመዛዝነው ውሳኔ መስጠትም ይችሉበታል።

„…አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻላል እንጂ… „ -ይህ ነው መልዕክቱን ከመቶ አመት በሁዋላ አሁን እንደገና ትኩስ አድርጎ እኛም እንድናነሳው ያደረገን አዲስ የሚያደርገውም- „…ትግሬ የብቻ ነው ሸዋ የብቻ ነው ቢገምድር ጎጃም የብቻ ነው እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ።…አሁን ስለእግዚአብሔር ብላችሁ እናንተም እርስ በእራሳችሁ ተፋቀሩ( ….) ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሣቂያ ትሆናለችሁ።“ የሚለውን ዓረፍተ ነገር ነውመርጠው በደብዳቤአቸው ላይ አስፍረዋል።

„ጎሣ መለየት“ የሚለው ቃልም „የአውሮፓ መሣቂያ እንዳትሆኑ „ ከሚለው ጋርም በትክክል አብሮ ተቀምጦአል።

ደብዳቤው ለአሁኑ የሃይማኖት አባቶቻችንትላንት የተጸፈም ይመስላል። ከእነሱም ጋር ወደውም ሆነ ሳይወዱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተገደው „ለተገነጠለቱም“ የኤርትራ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አብሮም የተሰነዘረ ይመስላል።

በዚሁ ሳቢያም ከእነሱ ጋር አብረው (ሳይወዱ)ለሄዱት ለካቶሊኩም ለውንጌላዊቱም፣ ለሞስሊም ሃይማኖት ተከታዮች ይመስላል።

አንድነት ተፋልሶ „እንደ ሽርሽር„የታየው „…መገንጠል“ ትዳር በብዙ ቦታዎች አፍረሶአል። ቤተሰቦች በትኖአል። ልጆችን አለወላጅ ወላጆችን አለልጆቻቸው አስቀርቶአል። ጦርነት ተከፍቶም ሥፍር ቁጥር የሌለው ሰው ከሁለቱም ወገን ሞተዋል።… ተበትነው ለሄዱትም ወገኖቻችን ደብዳቤው የተጻፈም ይመስላል።

ከሁሉም አሁን ቢሆን „ጌጥ“ እየሆነ ለመጣው ለዘር ክፍፍል አራጋቢዎች ከመጥፎ ሓሳባቸው ቆጠብ እንዲሉና እንዲያስቡበት የተወረወረም ማስጠንቀቂያ ይመስላል።

ጣይቱ „…ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሣቂያ ትሆናላችሁ“ ስሉ በተዘዋዋሪ የአደዋን ድል ለካህናቶቹ መልሰው ማስታወሳቸው ነው።

ቀደም ሲል ኢትዮጵያኖች ተለያይተው ሳይሆን ተባብረው አንድ ላይ ሁነው ተነስተው የውጭ ወራሪን መንግሥት ጣሊያንን ድል አድርገው በዓለም ሕዝብ ፊት-በአውሮፓ ትልቅ አድናቆትን እንዳተረፉ እቴጌይቱ በደንብ አዲስ አበባ ከተቀመጡ ልዩ መልዕክተኛ- አምባሳደሮች አፍ በእነሱ በኩል ስለ እኛ ምን በውጭ አገሮች እንደሚወራ ጥሩ አድርገው ያውቃሉ።

ለዚህም ነው ከአልጠፋ ነገር „…መሣቂያ“ አትሁኑ የሚለውን መልዕክታቸውን ደብዳቤአቸው ላይ ያሰፈሩት።

ወረድ ብለው አሳቢ እናትም ፖለቲከኛም መሆናቸውን እቴጌይቱ በደንብ – በዘመኑ በነበረው አነጋገር ግልጽ አድርገዋል።

„…እማሆይ ወለተ ተክሌ መቃብሬ ከዚያም ይሁን ብላ መጥታለችና አደራችሁን በምኑም በምኑም ነገር እንዳታሰቀይሟት። እንግዲህ ሷ እንዲህ አደረጉኝ ብላ የላከችብኝ እንደሆነ እንናንተንም እጠላችኋለሁ። እኔንም እንዳታስቀይሙኝ።“

ከዚህ ዓረፍተ ነገር ቀደም ሲል ስለ ዕርዳታ ገንዘብ ጉዳይ አንሰተዋል። „…ይህን ያህል መድከማችን ያንን ያህል ብር ባንክ አግብተን የዚያን ወለድ ከቤቱ የሚወጣውን ክራይ መስጠታችን እንዳትቸገሩ የሰው ፊት እንዳታዩ (…ነው) እንጂ ገንዘብ ተርፎን አይደለም።“

በአጭሩ „ …፩ነታችሁ እንዲጸና ብለን ነው እንጂ ገንዘብ ተርፎ ባገራችን በኢትዮጵያ ለምንሰጠው ሰው አጥተን አይደለም።“ የሚለው አረፍተ ነገር ትልቅ ትምህርት አሁንም ቢሆን ከአንድ መቶ አመት በሁዋላ የሚሰጥ ቃል ነው። እሱንም ብቻውን አላሰቀመጡትም። „ተስማሙ ተፋቀሩ“ አለበለዚያ….የሚለውን መልዕክት እቴጌይተዋ ጮክ ሳይሉ አብረው ሰደዋል።

„ስምምነት፤ ፩ ድነት፣ ፍቅርና ሃይማኖት … በሰው ፊትም ኢትዮጵያኖች መሣቂያ አለመሆንና ተቸግሮም የሰው ፊት (ልመና ማለት ነው) አለማየት „ አገሪቱ የተገነባችበት የቆየ ትሩፋት /ቨርቺውስ ናቸው።

መረዳት ለሚፈልግሰው የደብዳቤው መልዕክት ግልጽ ነው።

የጣይቱን ደብዳቤ ጊዜ እንዳነሳው፣ „አንድነትን „ የማይፈልጉትን ሰዎች አንድ ቀን ታሪክ አንስቶ እነሱን ይወቅሳቸዋል። በተለይ „፩ነታችን እንዳይጸና- የኢትዮጵያ „ የሚፈልጉትን ኃይሎች ጊዜ ሳይረሳቸው ይፋረዳቸዋል።

እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሜዳውን ይዘው የነበሩ ሰዎች „የልዩነት ቆጣሪዎች“ ነበሩ አሁን ደግሞ ዘመኑ ጊዜውም „የኢትዮጵያና የአፍሪካ አንድነት“ ፈላጊዎች ነው

ደብዳቤው መነበብ ብቻ ሳይሆን መሠራጨትም ያለበት ነው። ከታሪክ ሰነድ ፥ ጣይቱ ብልሂቷ (ደብዳቤ)

*

ለአእምሮየጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s