ካሲዮጵያና የ“ካሲዮጵያ ማህደር“

ካሲዮጵያና የካሲዮጵያ ማህደር

በግሪኮች ታሪከ፥ንግርት/ሚቶሎጊ እቴጌ ካሲዮጵያ የኢትዮጵያው መስፍንና ንጉሥ የንጉሡ የኬፊዎስ ሚስት ናት።

ከ -ካ ሲ ዮ ጵ  ያ    እስከ   መ ገ ነ ጣ ጠ ል /

ካ ሲ ዮ ጵ ያ

ከሁለቱም ትዳር ቤት አንዲት መልከ መልካም ውብ የሆነች ልጃቸው ልዕልት አንድሮሜዳ የሚባለውን ስም የያዘች ትወለዳለች።ልጅቱዋ ተወዳዳሪ የሌላት ቆንጆ ናት ይባልላታል።

ያም ሆኖ በቁንጅና እና በውበት በቁመናዋና በደም ግባቱዋ ግን በዚያች በኢትዮጵያ ምድር እናትዮዋን እቴጌ ካሲዮጵያ ማንም የሚበልጥ የለም በዚያን ዘመን አብሮ ይባላል።

እቴጌይቱም ይህን ስለምታውቅ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ላይ እኔን የሚበልጥ የለም ብላ የምትኩራራ ነበረች። እንዲያውም ከምድር አልፎ ማንም ቢሆን ከባህር ውስጥ ሆነ ወይም ከየትኛውም ትልቅ ውቅያኖስ በሰማይ ላይም ውብ ተፈልጎ ቢመጣ ከእኔ ጋር የሚስተካከል ማንም የለም ባይ ናት።

ቆንጆ ነኝ ብላ በዚያን ዘመን የምትኮራው ሌላ መልከ መልካም ውብ ልጅ ከውቅያኖሱ ንጕሥ ከኔሮይስ የምትወለደውን ልዕልት ኔርአይደን ነበረች። ይህች ልዕልት እቴጌ ካሲዮጵያ አንዴ አደባባይ ላይ ለሰው ሁሉ በይፋ የተናገረቺውን ነገር አሳዝኖአት ለአባቱዋ- አፈ-ታሪኩ እንደሚለው – ዝም ብለህ ታያለህ ወይ ላ አልቅሳ ታጫውተዋለች።

አባቱዋም ተበሰጭቶ ፖሳይዶን ለሚባለው አምላክ ጉዳዩን አይቶ እንዲፋረደው አቤቱታውን ለንጉሡ አንድ ቀን ያቀርብለታል።

ፖሳይዶን የአባትና ልጅ አዘኔታ ሰምቶ የባህር አሣነባሪዎችንና ዘንዶዎችን ልኮ ምድሩንና አካባቢውን በወሃ ጥፋት አንዴ ይመታውና ድብልቅልቁን ያወጣዋል።አገሪቱ የምትተርፈው ሕዝቡም ከወረደበት ማዓት አምልጦ ሰላም የሚያገኘው -ንግርት ተናጋሪዎችና ሕልም ፈቺዎች ያኔ እንዳሉት- የእቴጌ ካሲዮጵያና የኢትዮጵያው ንጉሥ የኬፊዎስ ውድ ልጅ ልዕልት አንድሮሜዳ ለዘንዶው ወይም ለትልቁ ዓሣ -ነባሪ መስዋዕት ሆና ስትሰጥ ነው ያኔ መረጋጋት ጠሚመጣው ብለው የታያቸውን ይናገራሉ።

„አገር ይጥፋ ወይስ አንዲት ልዕልት ትሙት?“ በዚህ አርዕስት ዙሪያ ብዙ ሕዝቡም መኳንንቱም መሣፍንቱም ተከራከሩ።

በሁዋላ ልዕልቲቱን ዓሣ ነባሪው ወይም ዘንዶው መጥቶ እሱዋን በልቶ ሰላም የሚሰፍን ከሆነ ትሰጥ ብለው ሁሉም ይስማማሉ።በመጨረሻው የባህሩ ዳር በሚገኘው አንድ ትልቅ ቋጥኝ ላይ አሥረዋት ከገቡበት ጣጣ ለመገላገል እሱዋን ጥለዋት ይሄዳሉ።

ዘንዶው ሳይደርስ አሞራዎች ሊገነጣጥሉወት ያንጃብባሉ። አውሬ ሊበሉዋት ያፏጫሉ።

በመጨረሻው ጀግናው ፔርሲዮስ ከንፎ መጥቶ ከዚያ የባህር አውሬ -ያቺን ልዕልት ብድግ አድረጎወስዶ -አፈ ታሪኩ እንደሚለው – አድኖአት በሁዋላ ተፋቅረው ተዋደው እሱ ያገባታል።

ከዚያን ዘመን ጀምሮ በጥንታዊው ዓለም ከእነዚያ ስምና ዝና ካተረፉት አርባ ስምንት ክዋክብት ውስጥ እቴጌ ካሲዮጵያ ባለዋ ንጉሥ ኬፊዎስ ልዕልት አንድሮሜዳና ፐተርሲዮስ ዘለዓለማዊ ሁነው ሰማይ ላይ ኮከባቸው በስማቸው ተመዝግበው እንዲያዙ ተደርጎአል።

በ17ተኛው ክፍለ ዘመን ብቻ ምን እንደሆን አይታወቅም „የካሲዮጵያን ኮከብ“ በመቅደላዊት ማሪያም ስም ለመቀየር ታስቦ ያ ሓሳብ በሥራ ሳይተረጎም እንዳው ተናፍሶ በዚያው ቀርቶአል።

እኛ ከንትርክ ነጻ– አድርገውን ወደፊት ሊያራምዱን የሚችሉንን የፖለቲካ አመለካከቶችና አቋሞች ከዛሬ ጀምሮ አንስተን እየፈታን „የካሲዮጵያ ማህደር“ ውስጥ ለመክተት አስበናል።

አንድ ውጤት ላይ ሳንደርስ – እንደ ከብት ሳር ሲመነዠግ፣ እንደማሲቲካ ሲታኘክ – እሰከ አሁን ድረስ አጅቦን ስለመጣው ስለ „ብሔር /ብሔረሰብ ጥያቄ…እሰከ መገንጠል ድረስ… „ በእሱ እንጀምራለን።

ለአእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6


መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s