ተስፋና ዕልቂት

ሞት ለላምፔዱዛ
ሞት በላምፔዱዛ፣ ሞት ለነጻ ሕይወት! ለነጻ-ኑሮ!

ተስፋና ዕልቂት

ሞት ለላምፔዱዛ

ሞት በላ ምፔዱዛ፣ ሞት ለነጻ ሕይወት! ለነጻ-ኑሮ!

ሰው ሲሞት፣ ማንም ሰው በከንቱ ሲሞት ያሳዝናል። እንዴት ነው የሞተው? ሲባል ደግሞ የሚሰማው መልስ አንዳንዴ አንጀት ይበላል።

የባህር ወሃ ሞገድ ሚዲትሬንያን ላይ መንገደኛን ሲበላ አዲስ አይደለም። የሰሃራ በረሃ ነጋዴንና መንገደኛን ከርሱ ውሰጥ ሲያስቀር እንደዚሁ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም።

ሰዎች ያን በረሃና ባህር ለመቋረጥ ሲጓዙ ይዘረፋሉ። ይገደላሉ። ሴቶች ብቻቸውን ከሆኑም ይደፈራሉ። ይህ አዲስ አይደለም።

ሰው እንደ በግ ታርዶ ሆድ ዕቃው ተከፍቶ ለታመሙ ሐብታሞች መለዋወጫ ሲሆን መስማቱ ግን ለእኛ አዲስ ነገር ነው። እዚያው ላይ ወንዶች ልጆች በወንዶች ሲደፈሩ ደግሞ መስማቱ ይህ ለእኛ አዲነገር ነው።

ባህሩን አቋርጠው ጣሊያኖች አፍሪካን ይዘዋል። አልፈውም ኢትዮጵያን ከአንዴሁለቴ አገሪቱን ለመግዛት ወግተዋል። አፍሪካውያኖችም-ሓኒባልም ዝሆን ይዘው ባህሩን አቋርጠው ጣሊያንን ወሮአል። ተመልሰው መጥተው ግን ሮማውያኖች እነሱን ፈጅተው ሰው እንዳይኖርበት ጨው ነስንሰው ድራሻቸውን አጥፍተዋል።

ዘንድሮ ግን የሚሰማው ሌላ ነው።

ንጉሠ-ነገሥቱን አሸንፈን፤ ደርግን ቀጥተን፣ አማራውን አሳይተን፣ ነጻ-ጋዜጣ አምጥተን፣ ነጻ-የሠራተኛ ማህበር፣ ነጻ-ፓርቲ ነጻ -ሽንጎ ነጻና -ዲሞክራቲክ ኤርትራን በአጭር ጊዜ አቋቁመን፣ እንደ ሲንጋፖርና እንደ ደቡብ ኮሪያ እንሆናለን፣በዚያም አገር እንመሰርታልን ብለው የተነሱት „ነጻ-አውጪዎች“ ከደርግ የባሰ፣ ብዙዎቹ እንደሚሉት ከሰሜን ኮሪያ ያለነሰ „አምባገነን በመፈጠራቸው“ ወጣቱ ትውልድ አገሪቱን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል።

እነሱ ብቻ አይደሉም።

እንደተነበበው፣ ከኢትዮጵያና ከሶሪያ ከኢራክና ከአፍጋኒሳታን፣ ከሱማሊያና ከሱዳን፣ ከሊቢያና ከቱኒዚያ፣ ከግብጽና …በቃን ብለው የሸሹ ሰዎችም ይገኙበታል።

ለምን? ምንነክቶአቸው ነው ሰዎች አገራቸውን ለቀው የሚሰደዱት?

አንድ ከሱማሌ ነፍሱን ለማዳንና ሕይወቱን ለማስተካከል የፈለገው ሰው እንዳለው- የተፈጠርነው መከራ ለማየት አይደለም- „እዚህ ብቀር እርግጠኛ ነኝ እሞታለሁ። ወደ አውሮፓ ጉዞዬን ባደርግ የመሞት ዕድሌ ቢያንስ ሃማሳ ለሃምሳ ነው። ከአልሆነልኝ መንገድ ላይ እሞታለሁ። ከተሳካ ደግሞ አውሮፓ እገባለሁ። እኔ ሞትን አልፈራም። ከፈለገ ደግሞ የማይቀረው ሞት ይምጣ!“ ብሎአል።

ሰዎች ተጨንቀው ይህን የመሰለ ደረጃ ላይ ደርሰዋል:- ሞትን የመጣው ይምጣ አልፈራውም እስከ ማለትም ሄደዋል።

ለምን አንድ ሰው በሕይወቱ ላይ ይፈርዳል?

ይህን ስንመለከት ጥፋተኛው ማን ነው ሊባል ነው?

እንደሚባለው የጣሊያን መንግሥት? ወይስ የአውሮፓ አንድነት ድርጅትና የአውሮፓ መንግሥታት? …ወይስ ደግሞ ምንም ነገር ወሃው ላይ ብታዩ አትርዱ የተባሉ ዓሣ አጥማጆች? ለመሆኑ ቀይ መስቀልም ጥፋተኛ ነው?

ዋና ተጠያቂ እላይ የተጠቀሱ አገሮች መሪዎች ናቸው። እነሱ ያቋቋሙት አስተዳደር።

ለምንድነው የጀርመን ኑዋሪዎች ተሰደው በመርከብ ሲጓዙ ሰመጡ የሚለውን ዜና ጥዋት ማታ በራዲዮ የማንሰማው? ለምንድነው አንድ አሜሪካዊ ወደ አፍሪካ በጀልባ ሲሸሽ ተገልብጦ ሞተ የሚባለው ወሬ በቴለቪዥን የማይነገረው? ለምንድነው አንድ እንግሊዛዊ ወይም የራሻ ስደተኛ ተወላጅ የሚድትሬኒያን ባህር ሲያቋርጥ ወይም ሰሃራ በረሃ ላይ ሲጓዝ የአፍሪካ አውሬ አንበሳ በላው በላቸው የማይባለው?

አሁን አይደለም ዱሮ ብልሃቱ ገና በአልገባቸው ክፍለ-ዘመን…. እንግሊዞች፣ ጀርመኖች፣ ጣሊያኖች፣ አይሪሾች፣ ግሪክና ፈረንሳዮች፣ ፖሊሺና …ድፍን አውሮፓ ረሃብ ገብቶ ሲጠብሳቸው፣ ችግር ሲያጠቃቸው፣ አረመኔ መንግሥት ሲገፋቸው፣ … መንደራቸውን ለቀው ተሰደው አሜሪካን ገብተዋል።

ስንቱን ያኔ ወሃ እንደበላው አናውቅም። ስንቱ በበሽታ እንደተቀሰፈ አናውቅም። ስንት ሴቶቹ እንደተደፈሩ የተጻፈ ታሪክ በእጃችን የለም። ወንዶች ሲደፈሩ ስንሰማ ግን የመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በኢትዮጵያ ፓስፖርት የዛሬ አርባና ሃምሳ አመታት ማንም እንደሚንቀሳቀስ ተንቀሳቅሶም አውሮፓ እንደሚጋባ በደንብ እናውቃለን። ይህን ዕድል ከአገኙት ውሰጥም የአሁኑ የአሥመራ ገዢዎች እንዳሉበት የታወቀ ነው።

በዚህ ፓስፖርት የኢትዮጵያ ተወላጅ ግሪኩም አርመኑም ሕንዱም ፓኪስታኑም የአፍሪካ ታጋዮችም ጭምር ማንም ሳይጠይቃቸው በይፋ በመርከብና በአይሮፕላን ይንቀሳቀሱ፣ ከዚያም አልፎ የዓለም አቀፍ ድርጅትም ውሰጥ ገብተው ይሰሩ እንደነበር ይታወቃል።

በኢትዮጵያ ፓስፖርት -የዛሬውን አያድርገው ያኔ ጀርመን አገርና ሌላ የአውሮፓ ከተማዎች አለ ቪዛ ይገባም ይወጣም ነበር።

ያ ዘመን ምን ይደረጋል:- አልፎአል።

አሁን „ሰው ሁሉ“ አገሩን ለቆ ሲወጣ ተጠያቂው ማን ነው? ለምንድነው አገራቸውን ለቀው እንዲወጡ የተገደዱበት ምክንያት?

ቁም ነገሩ ያለው እዚያ ላይ ነው። መልሱን ደግሞ ፈልጎ ለማግኘት ቀላል ስለሆነ ሁላችሁም ታውቁታላችሁ። ይህ ሁኔታ በጊዜው ካአልታረመ ነገ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እድላቸውን ሲሞክሩ መሞታቸው አይቀርም።

***

ሞት ለላምፔዱዛ

ሞት በላምፔዱዛሞት ለነጻ ሕይወት! ለነጻ-ኑሮ!

This slideshow requires JavaScript.

Source: http://www.stern.de/panorama/mittelmeer-vor-italien-kuestenwache-rettet-800-fluechtlinge-2066861.html

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s