አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

Advertisements

አፍሪካ እንዴት ሰነበተች

በሰሜን አፍሪካ በግብጽ የሚካሄደውን የፖለቲካ ውዝግብ ጋዜጠኖቹ ሳይረሱ፣ በማሊ የሚታየውን ትርምሶች ችላ ሳይሉ፣ ኮንጎን አይተው ሳያልፉ፣ ጅቡቲን ሳይዘሉ፣ ትላልቅ እዚህ አውሮፓና እዚያ አሜሪካ በየቀኑ እየታተሙ የሚወጡ ዕለታዊ ጋዜጣዎች፣ ያለፈው ወር „ድፍን ኬንያን ስለአናጋው“ የሽብር ፈጣሪዎች ጠለፋና ግድያ፣ ፍጅትና የቦንብ ፍንዳታ፣ ልዩ አተኩሮ ስጥተው ሁሉም ቅጠሎች ስለዚህ ጉዳይ በሰፊው ጽፈዋል።

ከዚሁም ዜና ጋር የሞገደኛውን -እዚህ እንደጻፉት-የቀድሞውን የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት የቻርልስ ቴለርን ሃምሳ አመት የእሥራት ፍርድ፣ ቦታውን ተሻምቶም እንዲወስድ አድርገዋል።

ስለሱዳን አመጽ አንስተዋል።በጎረቤት አገር በሱዳን የዋጋ መወደድን፣ የቤንዚን መጨመርን፣ ከዚያም አልፎ „የወታደሩ መንግሥት የፕሬዚዳንት አልባሽር አገዛዝ በቃን „የሚለውን „ሕዝብ እንቅስቃሴ“ የእነሱንም ታሪክ እነዚሁ ጋዜጠኞች ተገቢውን ቦታ ሰጥተው እኛን አስደስተዋል።

በቻርልስ ቴለር ላይ የቀረበው ዘገባና ሐተታ አንጀት ያርሳል። እሱም ይህን ይመስላል።

„ሃምሣ አመት ለቻርልስ ቴለር“ በሚለው አርዕስቱ ሥር የጀርመኑ ጋዜጣ ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ የሚከተሉትን ሓሳቦች ለአንባቢዎቹ በሐተታ መልክ አምዱ ላይ አሥፍሮ አንባቢዎቹ እንዲመለከቱት እነሱን ጋብዞአል።

„…የሕዝብ ድምጽና የሕዝብ ጩኸት፣ በላይቤሪያ ሰውዬውን ቀደም ሲል በትክክል ወንጀለኛ ነው ብሎ መስክሮበታል።“ ከአለ በሁዋላ ጸሓፊው ቀጥሎ„…ቻርልስ ቴለር ጦረኛ እና ሥልጣን የጠማው ሰው ነው።ከዚያም በላይ ይህ ሰው ጠብ ጫሪና እሳት ለኳሽ አደገኛ ፍጡር ነው፣ የሚለውን የቅጽል ሽሞች በግዛት ዘመኑም እሱ ያተረፈ ሰው ነው። ስለዚህ „ ይላል ጋዜጣው „…ፍርድ ቤቱ የተከሣሹን የይግባኝ ማመልከቻውን ተመልክቶ ውድቅ ማድረጉ፣ የሃምሣ አመት የእሥራት ፍርዱን ሳይሽርና ሳይቀንስ እሱን መልሶ አረጋግጦ በይኖበት አሁን ይፋ ማውጣቱና ይህን ማሳወቁ ትክክል ነው።…ፍርድ ቤቱ ግን …እግረ-መንገዱን በመረጃ ስብሰባ ላይ በርካታ የሚያጠያይቁ ክፍት የሆኑ ነገሮችን ማስተካከል መቻል ነበረበት።ይህን ግን አላደረገም። …ያም ሆኖ …ይህ በቻርልስ ቴለር የተበየነው ፍርድ ማንም የአፍሪካ መሪ እራሱን ከሕግ በላይ አድርጎ፣ በገዛ ሕዝቡ ላይ ከእንግድህ መጨፈር አይችልም።ፍርዱ ይህንንም ያሰየናል።“ ብሎ ጸሓፊው ሐተታውን በዚህ ዓረፍተ-ነገር ዘግቶአል።

„ሳይሽሩ፣ ፍርዱንም ሳያሻሽሉ…“ ሌላው የጀርመን ጋዜጣ „ዲ ኖየ ኦስናብሩከር“ ቀጠል አድርጎ እንዳለው“… እዚያው ብያኔ ላይ ዳኞቹ በመርጋታቸው ከእንግዲህ በምንም ዓይነት ወለም ዘለም የማይለውን አቋማቸውን ለሁላችንም ግልጽ አድርገውልናል።…ከእንግዲህ አንድ ጦረኛ እና አንድ ዲክታተር፣ አንድ አምባገነን ሥርዓት ወደፊት አለ ፍርድና አለቅጣት በሰራው ሥራ ሳይጠየቅበትና ፍርድ ቤት ሳይቀርብ አርፎ መተኛት እንደማይችል፣ ዳኞቹ ተስማምተው በወሰዱት እርምጃ በአሳዩትም ጥንካሬ ጥሩ አድርገው መጪውን ጊዜ ወዴት እንደሚያመራ ግልጽ አድርገዋል።…

በአለፉት አመታት በአፍሪካ ለረጅም ጊዜያት አምባገነኖችን ማንም ሰው ሳይከሳቸውና እነሱንም ማንም ሰው ፍርድ ቤት ሳያቀርባቸው የፈለጉትን ሥራ ሰርተው የልባቸውን አድርሰው ተቀምጠዋል። አሁን ግን በቻርልስ ቴለር ላይ በተወሰደው ቆራጥ ፍርድ፣ ይህ ነገር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሰሪያውን አግኝቶአል።

ይህ እራሱን አንዴ ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ከእሱም ገድላና የተአምር ሥራዎች ጋር የእራሱን ሥራ ድርጊትና ያወዳድር የበበረ ሰው አሁን ፍርዱን ተቀብሎአል…“ ብሎ በዚህ ሐተታው ከአንባቢዎቹ ተሰናብቶአል።

„ደር ሽፒግል“ የተባለው ትልቁ የሰሜን ጀርመን ሳምንታዊ መጽሔት ደግሞ በተራው „በዲሞክራቲክ የሩዋንዳ ነጻ-አውጪ ስም“ እዚህ ጀርመን አገር በስደት ላይ የሚገኘውን እዚያ በአገሩ- ክሱ እንደሚለው – የጦር እንቅስቃሴ የሚያካሄደውን የሽምቅ ተዋጊዎች ጦር ከእነድርጅቱ ትመራለህ ተብሎ ለተከሰሰው ለአንድ የሩዋንዳ ተወላጅ ዶክተር ኢግናስ ሙሩዋናሽያካ መጽሔቱ አምዱን ለግሶ ታሪኩን እንደዚህ አድርጎ አቅርቦአል።

„..ለአቅመ-አዳም ያልደረሱ ለጋ ወጣቶችን በማሰለፍ፣ ሴቶችን በመድፈር፣ የጦር እሳት በአገሪና በጎረቤት አገር በኮንጎ በመለኮስ ግዲያና ዝርፊያ በማካሄድ አንድ ትልቅ ሚና ትጫወታለህ ተብሎ ይህ ሰው ጀርመን አገር መከሰሱን መጽሔቱ ለአንባቢዎቹ ጽፎአል።

ወረድ ብሎም „በዚህ ኢ-ሰበአዊ ሥራቸው፣ ድርጊታቸው ከፍርድ ያመለጡ የሚመስላቸው ሰዎች መዝናኛ ቦታ እዚህ አውሮፓ እንደሌላቸው“ ከሌሎቹ ጋዜጣዎች ጋር በዚህ ወራት ይህን የመሰለ ታሪክ አምዱ ላይ አስፍሮ እሱም እንደተለመደ ከአንባቢዎቹ ተሰናብቶ ዞር ብሎአል።

ኒዮርክ ታይምስና ዋሽንግተን ፖስት፣ ዘኢንዲፔንደንተና ሔራልድ ትሪቢውን“…ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አገራቸው የገባችበትን ችግርና ቀውስ የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት ተገንዝቦ በእሳቸው ላይ የተመሰረተውን የፍጅት ክስና የቀጠሮ ቀናቸውን ፍርድ ቤቱ እንዲያስተላልፍላቸው የጠየቁት ጥያቄ ሰሚ ጆሮ አጥቶ ውድቅ ፍርድ ቤቱ እንደ አደረገው“ ዘግበዋል።

ሌሎቹ እዚሁ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ዴንሓግ የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት ተጋብዘው ይህንኑ ቃላቸውን በመስጠታቸው በአገራቸው በኬንያ የማስፈራሪያ ዛቻ በእነሱና በዘመዶቻቸው ላይ ስለወረደባቸው ምስክሮች በሰፊው ጽፈዋል።

ፍርድ ቤቱም ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ እንደጻፈው „…የምስክሮችን ደህንነት ለመጠበቅና የፍርድ ቤቱንም የምርመራ ሥራ ሳይሰተጓጎል በሥነ-ሥርዓቱ ለማካሄድ አስፈራሪ ሽብር ፈጣሪዎችን ኬንያ ድረስ ወርዶ እነሱን አሳዶ ለቅሞ እዚሁ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት አቅርቦ እነሱን ለመቅጣት አንድ ውሳኔ ላይ እንደደረሰም“ አያይዞ ዜናውን አንስቶአል።

የአስፈራሪ አምባገነኖች ዘመን በዚህ እርምጃ ቢያንስ የታገደ ይመስላል።

ፍርድና ፍትህ „የሰበአዊ መብቶች መግለጫ“ ላይ እንደ ሰፈረው ዓለም አቀፋዊ እየሆነ የመጣም ይመስላል።

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s