“ጃኖ” ውን ልበሱ
እኛ እነዚህን ወጣት ያገራችን የኢትዮጵያ የሙዚቃ ተዋናዮችን ስንተዋወቅ ደስ ብሎናል! የእነሱን ውብ አዳዲስየሙዚቃ ውጤቶች እያየንና እየሰማን የምናደንቀው፣ ለነጻነትና ለአዲስ ጥበብ ላዲስ ሕይወት የሚያደርጉት ጥሪ ሆኖም እንዲሰማን ስላደረገን ነው። በመሆኑም፣ ላንባቢዎቻችን እንዲተዋወቋቸው፣ እንዲያደምጧቸውና የነጻነቱ መንፈስ እንዲጋባባቸው እዚህ እንጋብዛለን!
እኛም፣ በያሬድ ቅዳሴና ዜማ አድገን ነፍሳችንን አውቀን፣ ከሌላው ዓለምና ከአዲሱ ዘመን ጋር ስንገናኝ፣ የነጻነትን መንፈስ በጊዜያችን ያበሰሩልንን፣ ከብዙ በጥቂቱ፣ የነጂሚ ሄንድሪክስን የነሳንታናን የነቢትልስንና ሮሊንግስቶንስን ቅኝት እያስታወሰን፣ እኛንም መለስ አርጎ ስለሚወስደን ብቻ ሳይሆን፣
የዚህ ዓይነት ተውኔትና ሙዚቃ ምን ያህል ነጻ የሆነ የሕሊና መንፈስ እንደሚያበጅም ስለሚገባን ነው!
ምን ያህል አእምሮንም ከፍ ወዳለ ቦታ ላይ እንደሚገፋውና እንደሚያደርሰው ስለምናውቅ ነው!
ስለሆነም፣ ይህን በሀገራችን የሙዚቃ ቅኝት ላይ የተመሰረተ አዲስ የኢትዮጵያ ተወዛዋዥ ቡድንን / Ethiopian rock & roll Band/ በርቱ፣ አዎ ደስ ደስ ይበላችሁ እንላለን! ደስታን የሚያውቅ ወጣት፣ ክፉ አዋቂ ሊሆን አይችልም!
እንኳን ደስ ያለህ እንላለን!
*
እንደውነቱ ከሆነማ፣ በኪነቱ አካባቢ ያሉትን ሌሎችንም (ለምሳሌ እንደ ወጣቱየሳሙኤል ይርጋ የኢትየጵያ ጃዝ ቅኝትና የግርማ ይፍራ ሸዋን ዓለም፥አቀፋዊ የክላሲካል ሙዚቃ ስኬት) ስናስተውል፣ እዚያው በዚያው የሚንደፋደፈው የፖለቲካው ማህበራዊ ክፍል ብቻ እንደሆነም እንገነዘባለን። ከገባበት የጦርነትና የአፈሙዝ ማጥ መላቀቅ ተስኖት፣ የነፃነቱን መንፈስ ሳያስተናገድ፣ ግማሽ ምዕተ ዓመት ትንሽም እምበር ሳይል አለፈ!
ለዚህም ይሆናል እነ ” ጃኖ “
” አይራቅ! አይራቅ! ” ሲሉ የሚጣሩልን!
ይሉናል! ይነግሩናል!
______________
እንዲያም ስለሆነ እንኳን ደስ አላቸው፣
እኛም በጥቂቱ እናወድሳቸው!
ኢትዮጵያን ከፍ አርገው፣
ኪነት ሙዚቃውን በማሻገራቸው…
ወጣት ደስ እያለው፣ እምበር እምበር ሲል
ሰማይን ፈልጎ ከፍ እያለ ሲዘል
በሙዚቃ ምሰጥ በኪነት ስነ ሀይል
ያስታውቃል ከሩቅ ነፃነትን ይሻል
“አይራቅ አይራቅ አይራቅ“ — ነፃነቱ ይላል!!
ጃኖ – ውን ልበሱ ….. ነፃነት ይመጣል፣
ወጣት ነፃ ሲሆን፣ „ጃኖን ባንድ“ ይመስላል!
*
ባለጃኖዎቹ፣ እንኳን ደስ ያላችሁ
ለዚህ ስኬታችሁ
ኢትዮጵያን አስጠሯት በሕይወት ፍቅራችሁ!
እውነት “መሄድ መሄድ፣ መ ሄ ድ “፣
መጓዝ ነው መፍትሄው ለነፃነት መንጎድ
ወጣት አይል አዛውንት
ሙዚቃችሁ ውበት ፈንጠዝያ ሕይወት!
ከፍ ባለው ሕሊና፣
*
እንኳን ደስ አላችሁ፣
እስቲ እናድምጣችሁ…
እስቲ እንያችሁ….
ተወዛወዙበት፣ ምስጋና ይግባችሁ!
እኛ እንኳን ዳር ቆመን እናመስግናችሁ!
*
http://janoband.com/fr_audio.cfm
****
አዲስ ገሰሰ
The Manager Introducing Jano Band
http://www.ethiotube.net/video/22907/Jano-Band–Who-are-they
*
—————————————————-
አስተያየት ለመስጠት / Comments
——————————–
——————–
© ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013