አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ዘዴ :-

አዲስ ትውልድ፣ አዲስ ዘዴ :-

“አዲስ ትውልድና አዲስ ዘዴ :-ስውር ኮሚቴ! ”

ይላል መጻጽፉ (1

ስምና አርዕሰቱ የመጽሐፉ እራሱ ብዙ ይናገራል። ፕሮግራሙና ዓላማው ግቡም ጭምር ምን እነደሆነ፣በአንድ ዓረፍተ ነገር ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል።

መጽሓፉን ያነበበ ቀርቶ ገረፍ ያደረገ ሰው አንዳንድ በቅርቡ የተካሄዱ ነገሮች ትዝ ይሉታል።

ለምን ቢባል:- የካይሮና የቲኒዚያ፣የብራዚልና የቱርክ ወጣቶች፣ የግሪክና የፖርቱጋል፣ የስፔንና የሮም ጎልማሶች፣ የስውዲንና የፓሪሶቹን የውጭ አገር ዘር ያላቸውን ልጆች …“በቃን!“ ብለው እንዴት፣ እንደተነሱ ምክንያቱንም ዘዴውንም እዚያ ውስጥ፣የፈለገ ሰው በቀላሉ ያገኛል።

የመጽሐፉ ደራሲ ወይም ደራሲዎች እንማን እንደ ሆኑ ሰማቸውን እላዩ ላይ ስለ አላሰፈሩ፣ እነ ማን እንደሆኑ አይታወቅም። እነሱም ሊታወቁ የፈለጉ አይመስሉም። …ስውር ናቸው?

ግን መጽሐፉን ለጥቂት ደቂቃዎች ጨብጦ ፣እያንዳንዱን ገጽ ያገላበጠ ሰው እንደሚረዳው ከእያንዳንዱ ምዕራፍ በስተጀርባ:-የአጻጻፍ ስልታቸው ፣የዓረፍተ ነገር አሰካካቸው፣የነገር አጣጣላቸው፣ እንደ ቅሉ የተለያዩ ስለሆኑ-ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ሰዎች፣ ሐሳብ በማመንጨቱ ላይ ሰብሰብ ብለው እንደተሳተፉበት በቀላሉ መረዳት ይችላል።

የፓሪሱን „ቃጠሎ“፣የስውዲኑን የወጣቶች ረብሻ፣የበርሊኑን „ከፖሊሶች ጋር የወጣቶች የአይጥና ድመት ጨዋታ“ ድንጋይ ውርወራና የእሳት ልኮሳ በመኪናዎች ላይ ጽሑፉ“አስክሮአቸው“ እንዲወጡ እነሱን እንደገፋፋቸው መገመትም አይከብድም።

„…የቀሰቀሱት እነሱ ደራሲዎቹ ሳይሆን አይቀሩም“ ተብለው፣ጋዜጣዎች ያኔ እንደጻፉት፣ አንዳንዶቹ በጥርጣሬ ተያዘው፣ ለአጭር ጊዜ የፖሊስ ምርመራ ተጋብዘው አድረውም እንደ ወጡ አንዳንዶቹ በአምዶቻቸው ላይ አሥፍረዋል።

በአጠቃላይ እነ ዩሊያን አሳኝጅን፣እነ ኤርዋርድ ስኖድንን፣እነ …እነዚያ ጥሩ ደመወዝ ይከፈላቸው የነበሩ ልጆች “… ምን አቅብጦአቸው ይህን ያህል ምሥጢር ሊያወጡና መንግሥታቸውን ሊያጋልጡ ቻሉ ?“ ለሚለው ጥያቄ ይህቺ ፓምፍሌት እንደ አቅምዋ መልስ ትሰጣለች።

ዱሮ (ይህ ነው አዲሱ ነገር) „የአንድ አመጽ“ አንቀሳቃሽ ቡድን መሪዎች፣የዚያ አላማ ጭንቅላቶች፣በስውርም ሆነ በይፋ የሚንቀሳቀስ አንድ „የፖሊት ቢሮ አባሎች፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ እጩዎችና መሪዎች፣…ጠቅላላ ጉባዔና ውሳኔዎች…“የሚባሉ የድርጅትና የአሰራር ዘዴዎች ነበሩ።

አሁን በእሱ ፋንታ „የማይታየው ሰውር ንፋስ“ (ይህ ነው እነሱ መርጠው የሰጡት የመጽሓፋቸው አርዕስት) ጠቅላላውን አመራር፣ሁሉንም ሥራ ይህ አካል እንዲይዝ፣እንዲጨብጥና እንዲወስድ እነሱ (ከጽሑፉ መረዳት እንደሚቻለው) አድርገውታል።

ይህን ይበሉ እንጂ አዝማች አለቃ ይህ ኮሚቴ የለውም።ሰብሳቢ ሊቀመንበር አያውቅም። የበላይና የበታች አካል፣የጦር አበጋዝና ሕዋስ፣አዛዥና ታዛዥ የለውም ። አይኖረውም።አይኖራቸውም። ታዲያ ምንድነው?

ትንሽ ጊዜ ወስዶ ጽሑፉን ጠለቅ ብሎ የሚያገላብጠው ሰው እንደሚረዳው ከሆነ „ሁሉም ሰው“ በመጨረሻ የእረሱ አለቃና አዛዥ፣ኮሚቴም ነው።

አላማቸው „ሥልጣን ላይ የተቀመጡትንና ሥልጣናቸውንና ጉልበታቸውን መከታ አድርገው በሥልጣናቸው የሚባልጉትን አምባገነኖች ከትከሻቸው ላይ“ እነሱ ጸሓፊዎቹ እንደሚሉት“ …በሕዝብ አመጽ እነሱን አራግፎ መጣል „ ነው።

ከዚያስ?

በእነሱ እምነት “ …ምርጫ አካሂዶ አዲስ ነጻ መንግሥት መመስረት፣ ለእሱም መምጣት መታገል ነው።“

„እሰከ አሁን“ ይላላሉ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት „በቃኝ ብላችሁ ተነሱእንጂ!“ የሚለውን ትንሽ ፓምፍሌት (መጽሐፍ) የጻፉት፣የፈረንሣዩ ዲፕሎማት፣ ስቴፋን ሔስል እንዳሉት “… የሰው ልጆች ፍረሃቻ ለአረመኔዎች አመችቶአል። …ብልሃቱ ግን ያለው እነሱን ደፍሮ መቃወሙ ላይ ነው…“ ብለው የእራሳቸውን የሕይወት ታሪክ ከሒትለር እሥር ቤት እንዴት እንዳመለጡ፣አምልጠውም የተቃውሞ ትግላቸውን እንዴት እንዳካሄዱ፣ አካሂደውም ለዲሞክራሲ ሥርዓት መመሥረት እንደታገሉ፣ ታግለውም በሁዋላም…ዓለም አቀፉን የሰበአዊ መብት አዋጅ አብረው ከሌሎቹ ጋር እንደነደፉ ከመሞታቸው በፊት እኝህ ሰው አጫውተዋል።

እሳቸው በዚህ „የማይታየው ሰውር ንፋስ ኮሚቴ“ በሚባለው ድርሰት ላይ ይሳተፉ አይሳተፉ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም።

ግን „ኦኩፓይ:-ሜዳውንም መንገዱንም፣ሰገነቱንም ያዝ“ የሚባለውን ዓለም አቀፉን እንቅስቃሴና የወጣት አረቦቹን ትግል፣በቱኒዚያና በግብጽ፣በየመንና በሊቢያ፣…እንደሚደግፉት ደጋግመው፣ከመሞታቸው በፊት እኝህ ጠንካራ ሰው ቀደም ሲል ገልጸዋል።

ለፖሊት ቢሮ ሰዎች፣ ለሴንትራል ኮሚቴ አምላኪዎች፣ ለፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ አካሎች፣ ለመረጃ ሰብሳቢዎች፣ ለተዋጊ ጦር አባሎች…እረ ምኑ ቅጡ፣ ለሁሉም ይህ“….ማንም ሰው ዛሬም ነገም በቤቱ ውስጥ ተቀምጦ ለእራሱ የሚፈጠረው ስውር ኮሚቴ..“ አስደንጋጭ ዜና ነው።

ለመያዝም፣ ለመቆጣጠርም፣ ለማገድም፣ ውስጣቸው ገብቶ ለመከፋፈልም አስቸጋሪም ነው። ይህ ያነጋግራል!

1)

https://mitpress.mit.edu/books/coming-insurrection


http://libcom.org/library/coming-insurrection-invisible-committee

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s