ዘ ጋርዲያን / The Guardian

ዘ ጋርዲያን / The Guardian

[1] የዛሬ 5000 ዓመታት ይህችን የነፃነት መልክት የነደፏት አስተዋዮች ምንኛ በደነቃቸው!

Advertisements

አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05/08-7

ብዙ ሐተታ አቅራቢ ጸሓፊዎች የኤድዋርድ ስኖውድንን መረጃ ሰነዶች እንቀማለን ብለው የ ጋረዲያንን መዝገብ ቤት አለማዘዣ ስለፈተሹት የጸጥታ ፖሊሶች እዚህ አውሮፓ ጽፈዋል።

እራሱ ዘ ጋርዲያን የደረሰበትን ችግር ከመካከለኛው ክፍለ-ዘመን ከኢንኩዜሽን ፍርድና ምርመራ ጋር አያይዞት የሚከተለውን አረፍተ ነገር ለአንባቢዎቹእንደዚህ አድረጎ አስፍሮአል።

„…እሰከ ዛሬ ድረስ ቀልዳችሁብናል። አሁን ግን ይበቃችሁዋል። የመጣነውም ሰነዱን ለመውሰድ ነው።´

በነዚህ ቃላቶች ነበር የብሪታኒያ መንግሥት በኢንተርኔት ክፍለ-ዘመን አስገራሚ የሆነውን የሳንሱር ቁጥጥር በእኛ ላይ ለመክፈት የቃጣው። በዝግጅት ክፍላችንም ጋዜጣችን የሰበሰበውን መረጃዎች የጸጥታ ፖሊሶቹ ልክ እንደ የቀድሞው የስፓንያን መጽፍ አቃጣዮች፣ በደስታ ዓይን ነበርእነሱም ተዝናንተው ሰነዶቻችን ሲወድሙ ይመለከቱት የነበረው።

የስኖውድን መረጃዎች በዓለም ዙሪያ እንደተበተኑ ብንነግራቸውም እንኳን፣ ከደስታቸው የተነሳ ይህን እርምጃችንን ሰምተው ከቁም ነገርም አልቆጠሩትም። የፈለጉት በመጥፎ መናፍስት ተያዙ የተባሉትን ሰዎች በእሳት ሲቃጠሉ ማየቱን ብቻ ነው። ሌላ እነሱ የፈለጉት እኛ ይህን የቃጠሎ ድርጊታቸውን እንድናከሽፍ ነበር።…እኛ ግን አውቀን ደስ እንዲላቸው ለቀቅንላቸው …“ ዘ-ጋርዲያን ይላል።

ቀደም ሲል ይኸው ጋዜጣ ” እነሱን የጎበኙ ነጭ ለባሽ ፖሊሶች፣ የጄምስ ቦንድ ፊልምን እንኳን በደንብ ያዩ ይመስላሉ” ብለው ቀልደውባቸዋል።

የጀርመኑ ጋዜጣ „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ ለምን ያለ ፍርድ ቤት ማዘዣ በሩን ለፖሊሶቹ ከፈታችሁላቸው ብሎ ጋዜጠኞን ሲወቅሳቸው፣ የራሻው ፕራቭዳ (ይህ ይገርማል) ከዚህ ቀጥሎ ያለውን ዓረፍተ-ነገር አምዱ ላይ አፍሮአል።

„ የጋዜጣው አዘጋጆቹ ያላቸው ምርጫ ውስን ነው። ወይ ሰነዱን አውጥቶ እነዳለ ሁሉንም ማተም ነው።ወይም እነሱ እራሳቸው መረጃዎቹን ማውደም።ወይም ደግሞ ጉዳዩን ፍርድ ቤት አድርሶ ከመንግሥት ጋር ጠበቃ ይዞ መሟገት ነው።

በሦስተኛው አማራጭ ላይ የፍርድ ቤት ዳኞቹም ሰነዱማጥናት ስለ አለባቸው መረጃዎቹ ምን ምን፣ ነገሮችን እነደ አዘለም ማወቅ ይችላሉ። ወጣ ወረደ ይህ ከሆነ ዘ ጋርዲያን ከቅጣት አያመልጥም ነበር። ስለዚህ ቀላሉ እና በገንዘብ ደረጃ ርካሹ መንገድ፣ የጸጥታ ፖሊሶቹ እያዩ፣ ሰነዱን ማውደም ትክክልኛ ውሳኔ ነው። እንደዚህ ዓይነቱ ድርጊት ደግሞ በጋርዲያን ታሪክ ፍጹም አስገራሚ ነበር።“

„አሁን የኮሚፒውተር ቀፎና ሆድቃውን ማቃጠልና መጨፍለቅ“ ኖይ ዙሪሸ ዛይቱንግ የተባለው የስውሲ ጋዜጣ እንደ አለው“… ምን ያደርጋል። በቀላሉ እኮ ጠቅ አድሮ ሥፍር ቁጥር የሌላቸውን ኮፒዎችና ግልባጮቹን ማንም ሊደርበት የማይችለበት አገሮችና መንደሮች ወይም አህጉሮች አሸጋግሮ ማስቀመጥ ይቻላል። ዋና አዘጋጁ አንድ ጥሩ ነገር ብሎአል። አስፈላጊ ከሆነ የተጠለፉትን ንግግሮችና ሰነዶች ሁሉ ወደ አሜሪካን አገር አሸጋግሮ ከዚያ ሁኖ (በአሜሪካን የፕሬስ በጣም ነጻና ሊበራል ነው) ማተም ይቀላል ነው፣ ብሎአል።“

የኖርዌዩ ዳግስአቪሰን በተራው፣ የብርትሺን ጸጥታ ፖሊሶች እርምጃ አውግዞአል።

„….እንዲያው ጉልበት ለማሳየት የተወሰደ እርምጃ ነው እንጂ ምንም ፋይዳ የሌለው ነገር ነው። ኃይልን ለማሳየት የብርቲሽ መንግሥት አውቆ ሕግን ተንተርሶ፣ አሳዛኝ የስልክ ጠለፋውን ድርጊት በዚህ ዘዴ አግዳለሁ ብሎ መድከሙ ከንቱ ነው።… ሕገ-ወጥ ሥራቸው ከተንኮል ሥራ የማይርቁትን፣ከእሱም የማይመለሱትን፣… ጨካኝ፣አረመኔ ገዢዎችን አለጥርጥር፣ በደንብ ያስታውሰናል። የጋርዲያንዋና አዘጋጁ የተናገረው ቃል ዕውነት አለው። የእንግሊዝ መንግሥት ህገ ወጥ ሥራአንድ የሚያሳየው ነገር ቢኖር ስኖውዲን የሰበሰባቸው መረጃዎች ምን ያህል ትልቅና ከባድ ቁም ነገሮች እንዳዘሉ ያሳያል

ጉዳዩ ለስርቦቹ ጋዜጣ “ፖለቲካ“ ለሚባለው ቅጠል ” በጣም አሳፋሪ ድርጊት ነው” ይላል።

„…የብሪታኒያ ጋዜጠኞች የምዕራቡ ዓለም እሰከ ዛሬ የሚኮሩበትን የፕሬስ ነጸነት፣ ሳይፈሩ ከፍ አድርገው በማውለብለባቸው ጥሩ ሥራ እነሱ ሰርተዋል። የየናይትድ እስቴት ኦፍ አሜሪካና ታላቁዋ ብርታኒያ በዚህ የሽብረ ፈጠራ ሥራቸው የዲሞክራሲ መሰረት የሆነውን የፕሬስ ነጻነትን ስም አድፈዋል። ጋዜጠኞቻቸው ሳይሆኑ እነሱ እራሳቸው በቀጠሩአቸው ሰላዮቻቸው መንግሥታቸውንና ሥርዓታቸውን፣ እነዚህ ሰዎች እንደሚያዳክሙባቸው አይገባቸው ይሆን?

…ስለዲሞክራምንም የማያውቁ፣ጭላንጭሉም እንኳን ቢሆን ምኑም በማይታይበት አገር፣ የሚሰሩና የሚንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች ከእንግዲህ ለእነሱ ወዮላቸው ማለት ይሻላል። በታላቁዋ ብርታኒያና በሌሎች የምዕራብ አገሮች የሚታየው የሳንሱር ቁጥጥር እነሱንዲሞክራየሚረግጡትን መንግሥታት ፣ይህ እርምጃቸው አደፋፍሮ ጋዜጠኞቻቸውን እንዲያዋክቡ የልብ ልብ -ተመልከቱ እነሱንም እያሉ- የፈለጉትን ለማድረግ ዕድል ይሰጣቸዋል። ያበረታታቸዋል።“

የቻይናን ጋዜጣዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እንደጻፉ ለመመልከት ሞክረን ሳይሳካልን ቀርቶአል።


[1]የነጻነት ሲምቦል (ca. 2350 B.C) /

http://sumerianshakespeare.com/21101.html

https://leaimero.files.wordpress.com/2013/04/a_schreibfeder.gif

አስተያየት ለመስጠት / Comments

——————————–

——————–

leaimero-reg-logo © ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements

Le’Aimero’s Disclaimer

——————–

አእምሮ መጽሔት፥ አዲሱ እትም – I-05/08-7

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s