ርሑስ በዓል ዒድ ኣልፈጥር
HAPPY EID ALFETIR
ዒድ ሙባረክ!
በዚህች የ ሁላችንም በሆ ነችው ውድ ሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዚህን መስመሮች ስንጽፍ፣ ለዘመናት ተከባብረውና ተቻችለው በመልካም ጉርብትና ደስታውንና የመከራውን ጊዜ እኩል ተካፍለው የሚኖሩትን የተለያዩ የሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችንን ለማጋጨት፣ በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ በሚፈጸመው ትልቅ በደል፣ ከፍተኛ ሀዘን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአሁኑ ሰዓት ይሰማናል። እንደዚህ ዓይነቱ በሌሎች አገሮችና አካባቢዎች የሚታዩት አሳዛኝ ግጭቶችም በአገራችን በኢትዮጵያ እንዳይስፋፋ፣ የምሁሩ ተግባር ብቻ ሳይሆን የማንኛውም ሰው ኃላፊነትና ግዳጅ ነው። ቸሩ ፈጣሪያችንም፣ እግዚአብሔር ከዚህ አደጋ ኢትዮጵያንና ልጆችዋን ይጠብቅ እያልን፣
መልካም በዓል !
ለሙዝሊም ወገኖቻችን ይሆንላችሁ ዘንድ ከልብ ለሁላችሁም እንመኝላችሁኋለን!
ርሑስ በዓል ዒድ ኣልፈጥር
HAPPY EID ALFETIR
ዒድ ሙባረክ!