“እንጀራ !…የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታወቃል” ይባላል። ዛሬ ኢትዮጵያ ሀገራችን የት እንደደረሰች፣ መለስ ብሎ ለማየት ብዙ ሃተታ አያስፈልገንም። ንጉሠ ነገሥቱን ለመጣል፣ እነሱ ያኔ አርቀው ያላዩትን፣ እንዲያውም የማያውቁትን፣ ብዙ ተንኮል ያዘለውና ኋላም፣ እነሆ ዛሬ፣ ታሪክ የሚመሰክረው፣ ብዙ መዘዝና ማአት ያስከተለውን፣ ተማሪዎች “ትግል በጀመሩበት ዘመን”፣ “ብዙ ተጋኖ የተነገረላቸውን” ሁለት ሰነዶች ፣ ምሁራኑ፣ ጉዳዩን ሁሉ መለስ ብሎ ብቻ፣ እንዲገነዘበውና እንዲያገናዝበው፣ እነዚህን ጽሑፎች ብዙ ፀሐይ ከሞቃቸው በኋላ መልሰን ዛሬ አትመናል።
ሎጂኩን ተመልከቱት። አረፍተ ነገር አጣጣሉን ልብ አድርጉት። የጽሑፉን አላማውና ግቡን አዳምጡት። መልዕክቱም ለምን እንደሆነ አስተውሉት። ከአርባ አምስት አመት በሁዋላ…
Walelign-on-the-National-question
——
________________________________