ኤጄርሳ ጎሮ
ሳይረሱ በየአመቱ እያስታወሱ ፣ እስከ ዛሬ ድረስ የልደት ቀናቸውን በይፋ የሚያከብሩት “ራስ ተፈሪያን”ብቻ ናቸው። እኝህ ንጉሥ ለአብዛኛው ተማርኩ ለሚለው “ተረማጅ” ኢትዮጵያዊ (ተራምዶ የት ተደረሰ?) እስከዚህም “ቦታ” የላቸውም።
እኛ ዛሬ የልደት ቀናአቸውን የምናነሳውና የምናስታውሳቸው፣ እኝህ ንጉሥ ለአገሪቱ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ፣ ለጥቁሩ ሕዝብ በሙሉ የሰሩት ሥራና ያበረከቱት አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን በመገንዘብ ነው።
ሁለተኛው ምክንያት “እሳቸውን ተክተን ለአገሪቱ ለኢትዮጵያና ለሕዝቡም ብሩህ ዲሞክራሲና ነጻ-ሕብረተሰብ እናመጣለን “ብለው የተነሱት (የተለያዩ ስሞች አሉአቸው) ቡድኖችና ኃይሎች፣ አነሱ በሙሉ፣ “ምን ፈጠሩልን” የሚለውንም ጥያቄ አንስተን ዓይናችንን ከፍተን እንድንመለከተውም፣ ይረዳል በማለት ነው። ለመሆኑ ምን የተሻለ አዲስ ነገር አመጡልን?
የሐምሌ 2005/ July 2013 ልዩ እትም ፣ ቀ.ኃ.ሥ – ቅጽ 1፣ ቁጥር 2
“የንጉሥ መብትን ያላከበረ ሥርዓት” አንዱ የጀርመን አዋቂ ፣ ማክስ ቬበር የሌንንና የስታሊንን አሰቃቂ እርምጃ በሩሲያ አብዮት ጊዜ ተመልክቶ እንዳለው ” …የንጉሡን ሰበአዊ መብትና ክብር የማያከብር አንድ ቡድን እንዴት አድረጎ የላብ አደሩንና የገበሬውን፣ የሌላውን ሰው መብትና ክብር ያከብራል?…ከዚያ ምንም አትጠብቁ “ብሎ ያስጠነቀቀውን ነገር፣ እግረመንገዳችንን አብሮም ለማስታወስ ነው።
እንግዲህ ነገር ጠርቶ የሚወጣው፣ እዚህ አውሮፓ እንደምናውቀው፣በተለያዩ ሓሳቦች:- በተጻራሪ አመለካከቶችና አስሰተሳሰቦች፣ በእነሱ መካከል ሁሌ በሚካሄደው ፉክክርና ሰላማዊ ክርክር ነው።
ከ”ሳይንቲፊክ ሶሻሊዝም ” ተገኘ፣ የተባለውን አንዱንም ሰነድ እዚህ እትም ውስጥ አብረን አያይዘን እንዲትመለከቱት አስፍረነዋል። ለኢትዮጵያ ያኔ የተነደፈው፣ “ዕውነታዊና” ፣ “ሳይንቲፊክ መፍትኄ” የተባለውን ! የት አደረሰን?
የትም የለም። ውሸት ነው።
መልካም ጊዜ
አዘጋጁ ይልማ ኃይለ ሚካኤል