ለ አእምሮ መጽሔት ስለ ፖለቲካና ኢኮኖሚ፣ ባሕልና ታሪክ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የሰኔ 2005 / June 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 4
የሰኔ 2005 / June 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 4
*******
የሕይወት አስትንፋስ :- ለእናት አገራችን ለኢትዮጵያ
______________________________
በዚህ እትማችን ሦስት አርዕስቶች ይዘን ቀርበናል።
- አንደኛው ፣ ካይሮ ላይ ስለ ተደገሰው ድግስ ነው። ያ ድግስ ምን እንደሚመስል፣ ደጋሹ ማን እንደሆነ ፣ የግብዣው ቢፌ መቼ እንደሚከፈት፣ ጽሑፉ ወረድ ብሎ ያብራራል።
- ሁለተኛው ፣ ስለ አዲሱ ትወልድ አስገራሚ የፈጠራ ችሎታ ነው። ወጣቶቹ ፣እንደምንሰማው መታገል፣ መቃወም፣ በቀላሉም መንገድ አሻፈረኝ ማለት ይችሉበታል። በአጭሩ “ሂድ ከዚህ ” በማለት በነገርና በተንኮል ተሳክረው ሕዝባቸውን መከራ የሚያሳዩትን “አምባገነኖች” በየአለበት አሁን እነሱ፣ ብልሃቱን አውቀውበት ችግር ላይ ጥለዋል። ቱርክ አንደኛው ነው። ብራዚል ሌላው ነው።ይህን መመልከቱም ጠቃሚ ነው።
- ዋናውና በሦስተኛ ደረጃ ፣ ቀጠል አድርገን፣ “ስለ አዲሱ ርዕዮተ ዓለም ” አንስተናል። ይህን ጀርመኖች እዚህ “ቬልት አንሻውንግ”/Welt-anschauung/ ይሉታል። ርዕዮተ፥ዓለም (ርዕዮተ፣ ራዕይ /Anschauung/ ከሚባለው የተወሰደ ነው) ፤ በሌላ ቋንቋ ” አይዲኦሎጂ” ተብሎ የሚታወቀው ነገር ነው። እኛ ደግሞ አእምሮዋችን የሚቃኘውና የሚቋጠረው፣ የኢትዮጵያ ራዕይ ላይ ሰለሆ ነ፣ እሱን “ርዕዮተ -ኢትዮጵያ” ብለን እንድ ጽሑፍ አዘጋጅተናል። በዚያውም ከዚሁ ጋር “ኢትዮጵያ” የሚለው አገርና ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ላይ በጽሑፍ ደረጃ ( ያኔ አሜሪካ የለም። እንግሊዝ አልተፈጠረም። ቻይና ወይም ደግሞ አሁን “ጌጥ “እየሆነ የመጣው… አማራና ኦሮሞ ፣ ትግሬና…ኦጋዴን ወይም እገሌና እገሊት የሚባሉ አጠራሮች በዚያን ዘመን አልነበሩም) ከአዳም መፈጠር ጋር ተያይዞ እንዴት፣ የሁላችንም አገር ስም የሆነችው “ ኢትዮጵያ “ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሰፈረ መለስ ብለን ጠቅሰናል። ለምን ይህ “ኢትዮጵያ”የሚለው ስም ከመጽሐፉ ላይ እንዲነሳ ሴራ እንደተጠነሰሰበት ግን አላነሳንም። ወጣ ወረደ ጽሑፉን መመልከት ይጠቅማል ። በእኛ ግምት ይህ “…ከየት መጣን?… እኛ ማነን ? ለሚለው ጥያቄም ፣ የሕይወት እስትንፋስ ለእኛ ብቻ ሳይሆን፣ ለሁላችንም ይሰጣል።
መልካም ቀን።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ዋና አዘጋጅ
__________________________________________
የሰኔ 2005 / June 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 4
____________________________________________________
- የሰኔ ወር 2005/ June 2013…እትም፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 4
- Documents:-
- U.S. Congressional Hearing: Ethiopia After Meles: The Future of Democracy and Human Rights.
- 2013 – Year of Pan-Africanism & African Renaissance
- Mubarak-Meles Agreement of July 1 1993
***
ለ-አእምሮ-መጽሔት-ቅጽ-1-ቁጥር-4-LeAimero-Vol-1-No-4 (በጥቅል/PDF) June 2013