„ሳይደግስ አይጣላም“
„ሳይደግስ አይጣላም“ ይላል አንድ በብዙ የሕይወት ተመክሮ ላይ የተመሰረተው የአገራችን አባባል። ይህ የአባቶች አነጋገር፣ ማመን ለማይፈልግ አንድ ሰው፣ ቢያንስ የቅንጣት ያህል፣ ትንሽ ዕውነት እንዳለው በዚህ ጽሑፋችን ለማስታወስ እንፈልጋለን።።
…የዋልድባ ገዳም መደፈር፣ …የሞስሊሞቹ የነጻነት ጥያቄ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ በድንገት በሞት መለየት፣ ….የግንቦት 25ቱ የሕዝብ ሰልፍ፣ አሁን ደግሞ የአባይ ውዝግብ፣ ….እነዚህ ሁሉን በአንዴ እና በተከታታይ፣ በአጭር ጊዜያት ውስጥ እናያለን ብሎ የገመተ፣ ሰው የለም።
በሌላ በኩል ፣ ከእንግዲህ ምን ይመጣል ብሎ ከመገመት ሌላ፣ በእርግጠኛነት፣ ይህ ይሆናል ያ ይደርሳል ብሎ ከአሁኑ ለመናገር አይቻልም። ይህን ለማለት፣ ከእሩቁም ለማየት፣ ነቢይ ወይም ጠንቋይ መሆንን ይጠይቃል።
እኛ በአለን „ዕውቀት“፣ ሁለቱንም ክፍሎች አንወክላቸውም። ግን፣ በአሁኑ ሰዓት አንድ ማለት የምንችለው ነገር ቢኖር፣ አንድ ሰው ወይም አንድ ድርጅት፣ አንድ ቡድን፣…. በእኛና በአገራችን በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ የሚወስንበት ጊዜ፣ በትክክል ደፍረን ለመናገር፣ ቀስ እያለ፣ ዘንድሮ በዚህ አመት እያከተመ የመጣ ይመስላል። ነጮቹ እንደዚህ ዓይነቱን ነገር፣ „ ዘ ቢግኒንግ ኦፍ ዘ ኢንድ ኦፍ ዛት ኤራ….“/The beginning of the end of that era…./ ይሉታል።
አሁንም ስለ ነጻነት፣ አሁንም ስለ የሕዝብ ጥያቄ ፣ አሁንም ስለ ፖለቲካ፣ እንደገና አሁንም እኛን የሚያለያየን ሳይሆን እንድ የሚያደርግን ነገር ምንድነው በሚለው ጥያቄ ዙሪያ፣ ይህን ጽሑፍ፣ ለአእምሮን አዘጋጅትን እንድትመለከቱት፣ አቅርበንላችኋል።
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
***
የሰኔ 2005 / June 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 3
ስለ ፖለቲካና ኢኮኖሚ፣ ባሕልና ታሪክ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የሰኔ 2005 / June 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 3
********************************
የሰሞኑ ሰነዶችና ጽሁፎች
——————————————————————————————————–
ለ አእምሮ መጽሔት፣ ወደ ዋናው ገጽ ለመመለስ…………………..
*
አድራሻችን ፥ Public Email
አስተያየት እንዲሁም ለአእምሮ መጽሔት ጥናቶችና ጽሁፎች ለማበርከት ፥ የሚከተለውን አድራሻ ይገልገሉ፥
Public Email
Verified Services
—————————————————————————————————————————
ሕግ፥ነክ ማስታወሻዎች / Disclaimer & Legal Statements:- Le’Aimero’s Disclaimer