ርዕሰ አንቀጽ
የትላንት ለዛሬው፤ የዛሬው ለትላንት ?
ጊዜ ይቀያየራል። የትላንት ለዛሬው፤ የዛሬው ለትላንት፣ እኛ ጋ ብቻ እስክመቼ ተደበላልቆ ይቆይ ይሆን? ዱሮ ፣ በጠራራ ጸሓይ ፣ የባንክ ካዝና በሽጉጥ አስፈራርተው የሚዘርፉ ወንበዴዎች እንኳን ፣ አሁን ሌላ ዘመን ውስጥ ስለገባን ፣ ከጊዜው ጋር ተራምደው፣ የዝርፊያ ስልታቸውን ቀይረዋል።
በፈረስ የሚመጡት፣ ካው ቦዮች፣ መኪና ይዘዋል። አሁን ደግሞ መኪናውንም ትተው፣ እዚህ መጽሔት ላይ እንደምታነቡት፣ በ21ኛው ክፍለ ዘመን፣ በባንክ ኤሌክትሮኒክ ካርድ፣ በቀላሉ ገንዘቡን ፣ ግድግዳው ላይ ከተለጠፈ የባንክ ካዝና፣ የፈለጉትን ያህል ብር ማስተፋት፣ ችለውበታል።
ዱሮ ዘማች ወታደሮችን አስታጥቀው፣ ድንበር አቋርጠው፣ በጦርነት፣ ሌላውን አገር መውረር የሚችሉ ኃያል መንግሥታት፣ አሁንም፣ ወረድ ብላችሁ እንደምታነቡት፣ በታጠቀ ሮቦተር፣ ልጆቻቸው ሳይሞቱ፣ሳይቆስሉ፣ ዘመናዊ ውጊያ ለማካሄድ ችሎታ እንዳላቸው አስመስክረዋል።
እንደዚሁ የ 18 ተኛው ሆነ የ19ኛው ክፍለ ዘመን አይዶኦሎጂም፣ እሱ ቀርቶ፣ የ20ኛው ክፍለ ዘመን ርዕዮተ ዓለምም እንደማይሰራ ብዙዎቹ ተረድተው፣ የፖለቲካ መስመራቸውን በጊዜው ቀይረዋል።
እኛም በ21ኛው ክፍለ-ዘመን፣ እባካችሁን የአረጀ የፈጀውን ቲዎሪአችሁን እዚያው የመጣበት፣ ጣሉና ለአገራችሁ ለኢትዮጵያ ፣ በዚህ መጽሔታችን ፣ እንደገና ልብ ገዝታችሁ አስቡ እንላለን።
መልካም ንባብ
—————