መልካም አዲስ ዓመት ! HAPPY NEW YEAR

እንኳን አደረሳችሁ !


እንኳን

አደረሳችሁ

ገና  ! X-MAS

ልጆች ሲጫወቱ ጣታቸውን እያሳዩና እየቆጠሩ „…እኛ ቤት ሁል ጊዜ ሁለት ገናዎች… ሁለት አዲስ ዓመቶች፣ሁለት ፋሲካና ሁለት… ይከበራል። ሁለቱንም ጊዜ ስጦታ ይቀርብልናል። ይሰጣናል።“

ይህን ሲሰሙ ሌሎቹ „ይህማ ትክክል አይደለም ! …እኛ እኮ አንዴ ብቻ ነው የምናገኘው ይህ ትክክለኛ ሥራ አ…“ 

„እንደ እናንተ!“-የበዓላችንን ብዛትና መደራረብ አይተው ነጮቹ- „ እንደ እናንተ የታደለ ሕዝብ የለም!“ ይሉናል።

እንደምናውቀው እኛም እርስ በራሳችን በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁለቴና ሦስት ጊዜ „…የደስታና የጤና የፍቅርና የሰላም ዘመን…ለአንቺም ለአንተም ለእኛም ይሁንልን ይሁንላችሁ!“ እንደ ደንቡና እንደ ቆየው ልማዳችን በሥነ-ሥርዓቱ እንባባላለን።

በእርግጥም ይህን ምኞት ማቅረቡና ማሰማቱ በደንብ ብናስብበት   (እንደ እኛ) ዕውነቱን ለመናገር – ምርቃቱ ቀላል አይደለም- የታደለ ሕዝብ የለም።

አዲሱን ዓመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ አብዛኛዎቻችን ውጭ አገር ያለን ሰዎች እናከብራለን። የገና በዓልን እንደዚሁ። ፋሲካንና ስቅለትን እነሱንም እንደዚሁ አከታትለን ሁለት ጊዜ አንዱ የእኛን ሌላ ጊዜ የአውሮፓን ከተለመደው የከበረ ሰላምታና ምኞት ጋር አብረን እኩል እናከብራለን።

ከሞስሊሙ ሓይማኖት ተከታዮችና ከአረቡ ሕዝብም ጋር እኩል  ትልቁን በዓላቸውን አብረን „…እንኳን አደረሳችሁ…“ ብለን በጋራ ተመኝተን በጋራ እናከብራለን።

ግን አንድ ቅር የሚልና የሚገርምም ነገር አለ። እሱም :-

በየጊዜው ለወዳጅ ለጓደኛ ለዘመድና ለጎረቤት „…የደስታና የሰላም የፍቅርና የጤና…ዘመን ይሁንልን“ ብለን የምንመኘው ምኞታችንን እግዚአብሔር ሰምቶ ለምን እስከ አሁን ድረስ ለዚያ „በመከራና በሥቃይ ለሚኖረው …ሰላምና ፍቅር ደስታና ጤና ለጠማውና ለሚናፍቀው ሕዝብና ለእኛም ጭምር  መልስ የአልሰጠበት መልስ  የማይሰጥበት ምክንያት ? ማወቁ አስቸጋሪ ነው።

ነጮቹ እንደሚሉት በእርግጥ „እሱ ረስቶን“ ይሆን?

ወይስ ሌሎቹ እንደሚሉት „ምኞቱ ከልብ ስለአልሆነ …አልሰማ ብሎን ይሆን?“

ይህን የምንልበት በቂ ምክንያት አለን።

ፍቅሩም ሰላሙም ጤንነቱም (በየአለበት ሰው ሁሉ በነገር ተሳክሮ ዕብደት  ብቻ ስለሆነ) ይኸው የተባለው ምኞት ሳይደርስልን ከአርባ አመት በላይ ስንቆጥረው አልፎታል።

„…ኤርትራ ትገንጠል፣…ኤርትራ ከአልተገነጠለች፣… ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም። ስለዚህ ኤርትራ ይኸው በእናንተ ፈቃድና ምኞት ትገንጠል ብላችሁ ጠይቃችሁ ተገነጠለች። እኛም ይህ ከሆነ ከእንግዲህ ውጭ የሚንከራተት የኤርትራ ስደተኛ አይኖርም። ጦርነቱም ያቆማል። ወደፊትም አይኖርም ብለን ገምተን ነበር። ግን አሁን እንደምናየውና እንደ ምንሰማው ሰው በብዛት አገሩን እየጣለ እየወጣ የስደተኛው ቁጥር በውጭ አገር ጨምሮአል።… ይባስ ብለችሁ ኦሮሚያ ከአልተገነጠለች ትላላችሁ። ኦጋዴን ከአልሄደች። አማራ መንደሩን ለቆ ይውጣ ከማለት አልፋችሁ ደግሞ የእራሳችሁን ትላልቅ ለም የእርሻ መሬት ከነጫካውና ከነወንዙ ለባዕድ መንግሥታትና ነጋዴዎች  ለሰባና ዘጠና አመታት ቸብችባችሁ፣ በረሃብ አለቅን ልናልቅ ነው እረ እባካችሁ ድረሱልን ትላላችሁ። …ምንድነው ለመሆኑ እናንተ  የምትፈልጉት? ለመሆኑ የምትፈልጉትን በቅጡ ታውቃላችሁ….“  ነጮቹ እንደዚህ እያሉ በየጊዜው ይጠይቃሉ።

ዕርዳታ አቅራቢ ነጮቹ የፈለጉትን በየጊዜው ይህን ሲሉ ዕውነት አላቸው።

ታሪክ ፍርዱዋን ያልሰጠች ይመስል– ታሪክ ፍርዱን ብዙ ቦታ ሰጥቶአል– ንጉሡ ወርደው በንጉሡ ፋንታ„…ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩበት ነጻ ምርጫ የሚካሄድበት ነጻ-ሕብረተሰብ በኢትዮጵያ ይመሰረታል „ እንዳልተባለ በእሱ ቦታ የተረሣውን መድገም ያስፈልጋልደርግ የሚባል የወታደሩ አምባገነን መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ ተመሥርቶ ሁሉን ጸጥ ለጥ አድረጎ ገዝቶአል።

ለማስታወስ ያኔም በየዓመቱ ለአሥራ ሰባት ዓመታት በተከታታይ„…ገና ሲመጣ ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ…ፋሲካ ሲደርስ እንደ ተለመደው „…የሰላም የፍቅር የ…“ ተባብለናል።

በሁዋላስ?

እነሱን -ደርግንና መንግሥቱ  ኃይለማሪያምን ጥለን- „ …እንደገና ነጻና ዲሞክራቲክ መንግሥትን በኢትዮጵያ መስርተን የግለሰብ ነጻነትን አክብረንና አስከብረን ነጻ-ጋዜጣን ፈቅድን የፓርላማ ምርጫን አካሂደን …“ ያሉ ድርጅቶች ሥልጣኑን ሲጨብጡ አገሪቱን ለሁለት ከፍለው መዳፋቸው ውስጥ አስገብተው ትንሽ ቆይተው እነሱ እራሳቸው ጦርነት ከፍተው ከአንድ መቶ ሺህ ወጣቶች በላይ ባድሜ ላይ ወድቀዋል።

እንደገና ለማስታወስ ያኔም እንደተለመደው „…እንኳን አደረሳችሁ ተባብለን…የፍቅርና የሰላም የደስታና የ…“ ምኞታችንን ተለዋውጠናል።

አሁንስ?

በሥልጣን ዘመናቸው ቅንጣት ያህል እንኳን አተኩሮ አድረገው „…የሰበአዊና ዲሞክራቲክ መብቶችን ጉዳይ ዞር ብለው ያላዩ ሰዎች“ አንዱ እንዳለው (እነ አቶ ታምራት ላይኔ እነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አቶ ሰዬ አብረሃ፣አምባሳደር ካሣ ከበደ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ…)አሁን ሰውዬው እንዳለው „ ለዲሞክራሲ መምጣት ግንባር ቀደም ታጋይ ወጥቶአቸው እኛን ከገባንበት ማጥ ነጻ ለማውጣት ተነስተዋል“

ከፊሉ አሥመራ ላይ መሽጎ! ሌላው ከአሜሪካየተቀረው ከአዲስ አበባ !

„ለመሆኑ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ?“ ብለው አንዳዶቹ እራሳቸውን ተገርመው ይጠይቃሉ።

„የሞቀ ቤታቸው ውስጥ ተቀምጠው“ ነጻውን የዲሞክራሲ አየር የሚተነፍሱ እንደፈለጉ ማንንም ሳይፈሩ ገብተው የሚወጡ አንዳንድ ሰዎች ደግሞ -ይህ ነው ሌላው ጥያቄ „…ለምን እና በምን ምክንያት ምንስ ነክቶአቸው ነው ? …ስለ ኪዩባና ስለ ፔኪንግ ስለዚያ አምባገነን ሥርዓት ስለ እነሱ መፍትሔና ጎዳና ለአገራቸው ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቻቸኙት?“ ብለው ነጮቹ እዚህ በሚያወጡት ጽሑፍ ላይ እራሳቸውን ይጠይቃሉ እኛንም መልስ አምጡ ብለው ይወተውታሉ።

አልፈው ሄደው በነገሩ ተገርመው “ …ከአልጠፋ የሰበአዊና ዲሞክራሲዊ መብቶች ጽንሰ-ሐሳብ ኮንሴፕት (ዓለም አቀፉ የተባበሩት መንግሥታት አዋጅ አለ) ለምንድነው አንዳንድ ጸሓፊችከአልጠፋ ነገር ስለ `የገዳ – ዲሞክራሲ´ና ስለ እሱ መምጣት የሚያስተምሩት?“ ብለው እነዚህ ሰዎች እራሳቸውን ይጠይቃሉ።

እንግዲህ „አትድከሙ እግዚአብሔር ረስቶአችሁዋል።„ የሚሉት ወገኖች ሆነ ወይም „….ቅመሱት እኛም ቀምሰነው ወጥቶልናል …..ይገባችሁዋል „ የሚሉት የቀድሞ ምሥራቅ ጀርመን ወዳጆቻችን…  ሁለቱም ሦስቱም ወቃሾች ሁሉም በእኛ ላይ በሚሰጡት „ፍርድ“ ዕውነት ያዘለ ነገር የወረወሩ ይመስለናል። ዕውነትም አላቸው።

„…የሰላምና የፍቅር፣የደስታና የጤና የብልጽግና እና የጥጋብ የጸጋና የሐብት…“ ምኞቶችን ከልብ ታስቦበት ለዘመድ ወይም ለወገን ከአልተመኙላቸው፣ያ ነገር ዝም ብሎ ከተፍ አይልም። መመኘት ብቻ ሳይሆን ያ የተመኙት እንዲመጣም እንዲደርስም በፍቅርና በአንድነት በጋራ አንድ ላይ ሁነው ተረዳድተው ተግተው ጥረው ደክመው እንደገና በጋራ ያ ሁኔታ እንዲመጣ ከአልሰሩበት እንዲያው ከሰማይ ዱብ የሚል የመና ዳቦም አይደለም።

ምናልባት „እግዚአብሔር የማይሰማን እሰከ አሁን ያልሰማን „ ከልብ ስለአልሆነ ይሆን?

ታሪክ ፍርዱዋን ሌላ ቦታ ሰጥታለች።

 ዞር ብለን አካባቢአችንከቃኘን  ብዙ ቦታዎች ታሪክ ፍርዱዋን ሰጥታለች።

አካባቢአችንከቃኘንና ትንሽ ቆም ብለን ደግሞ እሱን አንስተን ከአሰላሰልን አንድ የምንረዳው ነገር ቢኖር  „… የበለጸጉ ሓብታም የእንዱስትሪ አገሮች የሚባሉት መንግሥታት“ እዚህ የተረፈ ዳቦ የሚጣልበት ደረጃ ላይ የደረሱት፣  እነሱ ከእኛ ይልቅ „…አማኝ ሃይማኖተኛ ሁነው  እግዚአብሔርን በመቅረባቸው ብቻ „ተባርከው እዚህ የደረሱ ምርጥ ልጆቹ“ በመሆናቸው አይደለም።

 ወይም  ደግሞ አንዳንዶቹ እንደሚገምቱት „እኛ ተረግመን ለማኝ ሆነን እንድንቀር የተደረግን ፍጡሮችም“ አይደለንም።

ቁም ነገሩ ያለው ሌላ ቦታ ላይ ነው።

እነሱ ፣- ይህ ነው የኑሮ ብልሃቱ- እነሱን ከሚያጣላና ጥላቻን ብቻ ከሚያስተምር አይዲዎሎጂ እና የፖለቲካ ቲዎሪ እረሳቸውን አርቀው ተቻችለውና ተከባብረው -እኛ ሁላችንም በየአመቱ አንዴ ወይም ሁለቴ እንደምንለው „…የሰላምና የፍቅር የደስታና የብልጽግ  የጤናና የፈንጠዚያ …ምኞታቸውን“ በቃላትና በአፍ ብቻ ሳይሆን በተግባር በሥራ ላይ አውለው በጋራ አንድ ላይ ቆመው ተደጋግፈው በመሥራታቸው ብቻ ነው። ተግባባን?

ይህ ደግሞ ፈጠራ ሳይሆን የፖለቲካ ቲዎሪ መጽሓፍቶቻቸው ውስጥ ተጽፎ ይገኛል።

ይህን የጋራ ዓላማ የሚጥስ ሰው በመካከላቸው የለም ፈጽሞ አይገኝም ማለት አይቻልም። ግን -ይህን ማወቅ ያስፈልጋል- ሕጉም ሞራሉም ሕሊናውም ነጻ-ፕሬሱም አስተዳደጉም ጓደኛውም፣ ዘመድም ወገንም የሁዋላ ሁዋላ እንደዚህ ዓይነቱን ሰው ይወቅሰዋል።ይገሥጸዋል። ተው እንዴ አበድክ ወይ ይለዋል።   

በዚህ መንፈስበዚህ አመለካከት እንኳን ለአዲሱ አመት እንኳን ለብርሃነ ልደቱ፣ ለሰላምና ለፍቅሩ … በደህና አደራሳችሁ እንላለን።

የሰላምና የፍቅር የደስታና የብልጽግና  የጤናና እና የፈንጠዚያ ዘመንም እንመኝላችሁዋለን!

ምናልባት  ፈጣሪያችን – ይህን ከልብ ስለአልን- አንድ ቀን ይሰማን ይሆን?

አዘጋጆቹ
*

ለ አእምሮ ልዩ  እትም / ታህሳስ/ጥር 2006 / 01 / 2014 – አዲስ ዓመት/ ቅጽ 2፣ ቁጥር 5

**

 

ለ አእምሮ የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳግማዊ ምኒልክ – ቅጽ 2፣ ቁጥር 4/

ለ አእምሮ / Le'Aimero የህዳር 2006/ November/December 2013 እትም / – ዳ

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

( A New Book)

“Abyssinian Christianity: The First Christian Nation?”

መልስ ካሎት/ Reply (to comments):

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s